ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በኩዌት መሪ ሕልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለፁ

የኩዌት መሪ ነዋፍ አል-አሕመድ አል-ጃብር አል-ሰባህ

ታህሳስ 6/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኩዌት መሪ ነዋፍ አል-አሕመድ አል-ጃብር አል-ሰባህ ህልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት የኀዘን መግለጫ፥ ለሟች ቤተሰቦች እንዲሁም ለኩዌት ሕዝብና መንግሥት መፅናናትን ተመኝተዋል።