ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

ሚያዝያ 26/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ልዩ መልዕክተኛ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ልዩ መልዕክተኛን ዛሬ ከሰአት በኋላ ማነጋገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ተፋላሚ ኃያሎች ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ጥሪያችንን አቅርቤያለሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሱዳን በልጆቿ ጥበብና በሳል ንግግር አሁን ካለችበት ሁኔታ ባጠረ ጊዜ እንደምትወጣ ኢትዮጵያ ያላትን ዕምነትም አረጋግጫለሁ ብለዋል።