ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከሳዑዲ ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሳዑዲው ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ

ጥቅምት 30/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲ ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ ጋር ተወያዩ፡፡

በሁለትዮሽ ስብሰባ ከሳዑዲ ልዑል መሃመድ ቢን ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ ጋር ዛሬ ከሰዓት በኋላ በመወያየታችን ደስታ ተሰምቶኛል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በውይይታቸው የኢትዮጵያን የልማት እና የኢኮኖሚ ሪፎርም ብሎም በቀጠናው እየተጫወተች ያለችውን ሚና ጨምሮ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ተነስተዋል፡፡

“ሁለቱ ሀገሮቻችን በትብብር ልንሰራባቸው የምንችል ብዙ ስትራቴጂያዊ ፍላጎቶች አሉን።” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር).

ከዚህ አኳያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚቴ ለማቋቋም፣ በሳዑዲ ወገንም የዕዳ አከፋፈልን ሁኔታ በማሻሻል፣ በኃይል አቅርቦት ትብብር ብሎም በልማት ፋይናንስ የኢትዮዽያን የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እንድትደግፍ መግባባት ላይ ተደርሷል ነው ያሉት።