ጠ/ሚ ዐቢይ ኢትዮጵያ የተገበረችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ትልቅ ለውጥ አስመዝግቧል አሉ

ኅዳር 20 /2015 (ዋልታ) ኢትዮጵያ የተገበረችው የዲጂታል ኢኮኖሚ ባለፉት አራት ዓመታት በኢኮኖሚው እና ማህበራው ዘርፍ ትልቅ ለውጥ ያስመዘገበ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በ17 ኛው የበይነ መረብ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

በበይነ መረብ ያልተገናኙ ህዝቦችን ማገናኘት እና የበይነ መረብ ጥራት ላይ ኢትዮጵያ በርካታ ስራ መስራቷን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ውስጥም የአምስተኛው ትውልድ ኔትወርክ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ የሰራቻቸውን ስራዎችን አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን የሀገር ጥቅም ለማስጠበቅ እና ደህንነትን ለማረጋገጥ እየተጠቀመችበት እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

ዘርፉን በግብርና እንዲሁም በጤና እና በትራንስፖርት የአገልግሎት ዘርፎች ላይ ተግባራዊ በማድረግ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል፡፡

በሄብሮን ዋልታው