ጠ/ሚ ዐቢይ ከአማራ ክልል ተወካዮች ጋር ተወያዩ

የካቲት 11/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአማራ ክልል ሁሉም ዞኖች ከተውጣጡ ተወካዮች ጋር በክልሉ የገጠሙ ቁልፍ ጉዳዮችን አስመልክተው ውይይት አደረጉ።

በአማራ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በመላው የክልሉ አካባቢዎች በብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የተደረገውን ውይይት ተከትሎ ነው ውይይቱ የተካሄደው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው በውይይቱ ወቅት በቀረቡ በርካታ ጉዳዮች ላይ ምላሽ በመስጠት ለጋራ አላማ የጋራ ጥረት የማድረግን አስፈላጊነት በአፅንዖት አንስተናል ብለዋል።