ጠ/ሚ ዐቢይ ከአሜሪካ የንግድ ዘርፍ ተወካይ ጋር መከሩ

ታኅሣሥ 6/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካ የንግድ ዘርፍ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ጋር መከሩ።

በዋሽንግተን እየተካሄደ ባለው የአፍሪከ- አሜሪካ ጉባኤ ላይ ለመታደም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአሜሪካ የሚገኙ ሲሆን ከጉባኤው ጎን ለጎን ከበርካታ ሀገራት መሪዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች ጋር እየተወያዩ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካ የንግድ ዘርፍ ተወካይ አምባሳደር ካትሪን ታይን ጋር የኢትዮጵያ እና አሜሪካን የንግድ ትስስር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን በቲውተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል፡፡