ጠ/ሚ ዐቢይ ከፈረንሳይና ጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

ጥር 4/2015 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካትሪን ኮሎንና እና ከጀርመን የፌደራል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባየርቦክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሰፈሩት ጥልቅ እና ፍሬያማ ውይይታችን ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ጋር ያላትን ጠንካራ እና የቆየ ግንኙነትን የሚያንፀባርቅ ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት እያከናወነች ያለችውን ዘርፈ ብዙ ማሻሻያ፣ ቁልፍ ውጤቶችንና ተያያዥ ችግሮችን ለሚኒስትሮቹ አካፍለዋል።

ኢትዮጵያ ከፈረንሳይ እና ከጀርመን ጋር ያላት ግንኙነት ለበርካታ አሥርት ዓመታት ቆይቷል።

ባለፉት አራት ዓመታት ከሁለቱም ሀገራት ለተደረገው ያልተቋረጠ ድጋፍ እመስግነዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮችም ለውጡን ለማስቀጠል የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።