ፈቲያ ኦስማን የ2023 የዓለም ሬንጀሮች ሽልማት አሸነፈች

ሬንጀር ፈቲያ ኦስማን

ሐምሌ 19/2015 (ዋልታ) የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ሬንጀር የሆነችው ፈቲያ ኦስማን የዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ህብረት ዓለም አቀፍ የሬንጀሮች ውድድር አሸናፊ ሆናለች።

በኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ባለስልጣን መስሪያ ቤት በተካሄደው ቨርቿል የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኩመራ ዋቅጅራና ተሸላሚዋ እንዲሁም የመስሪያ ቤቱ ባልደረቦች ተሳትፈዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ፈቲያ በማሸነፏ ደስታቸውን ገልጸው የባቢሌ ዝሆኖችን ለመታደግ በሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ፈቲያ ከ50 አገራት የተውጣጡ ከ140 በላይ ተወዳዳሪዎች በተሳተፉበት መድረክ ነው ሽልማቱን ያሸነፈችው።

በልዩ ልዩ ዘርፍ የተወዳደሩ በርካታ ሬንጀሮች የተሸለሙ ሲሆን ከአፍሪካ ፈቲያን ጨምሮ ሁለት ሬንጀሮች መሸለማቸው ታውቋል፡፡

በቴዎድሮስ ሳህለ