ፓርቲው ከቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማማ

ቻይና የተጓዘው የብልፅግና ፓርቲ ልኡካን ቡድን አባላተተ

መጋቢት 25/2016 (አዲስ ዋልታ) ለአንድ ሳምንት በቻይና ጉብኝት ሲያደርግ የነበረው የብልፅግና ፓርቲ ልዑካን ቡድን ከቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ (ሲፒሲ) ጋር በልዩ ልዩ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ መድረሱ ተገለጸ።

በልምድ ልውውጥ ጉብኝቱ ወቅት ከቻይና ኮሚዩኒስት ፓርቲ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምክትል ሚኒስትር ሊ ሚንሺያንግ እና ከኒንሺያ ክፍለ ሃገር አስተዳሪ ሊያንግ ያንሹ ጋር በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይቶች ማድረጋቸውን የብልፅግና ፓርቲ ህዝብ እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አዲሱ አረጋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

አዲሱ አረጋ-የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ኃላፊ 

በውይይታቸው አንደኛው ጉዳይ የአመራር አቅም ግንባታ፣ በኢትዮ-ቻይና የባህልና ቱሪዝም ልማት ተሞክሮ ልውውጥ፣ የኢኮኖሚ ልማት አጋርነትን ስለማጠናከር እንዲሁም በቻይና እና ኢትዮጵያ የከተማ ከከተማ እና የክፍለ ሃገር – ከክልል የእህትማማችነት ግንኙነት በመፍጠር በሚሉ አራት ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ልዑካን ቡድኑ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቹው አካላት ጋር ተከታታይ ውይይቶችና የመስክ ጉብኝቶችን ማካሄዱንም ነው የተገለጸው።