ፕሮፌሰር ሂሩት ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ልዩ ዕጩ ናቸው – ጠ/ሚ ዐቢይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት በእጩነት መቅረባቸውን እንደሚደግፉ እና ለኮሚሽኑ ልዩ ዕጩ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቢኔ፣ በሳይንስና በከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሚኒስትርነት ያገለገሉት ፕሮፌሰር ሂሩት በሚኒስትር ማዕረግ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪነት እያገለገሉ መሆኑን፣ ገልጸው ኢትዮጵያን በመወከል ለአፍሪካ ህብረት የትምህርት፣ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኮሚሽነርነት ልዩ እጩ ናቸው ሲሉ ነው በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው የገለጹት፡፡