የእንግሊዝ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ እየተገነቡ ባሉ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንደሚገቡ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21/2008(ዋኢማ)-የእንግሊዝ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያሳድጉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጥሪ አቀረቡ።

ሚኒስትሩ ከእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ ልዑክ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ በሁለተኛው የዕቅድ ዘመን በልዩ ትኩረት በምትሰራባቸው በኢንዱስትሪ ልማትና በአቅም ግንባታ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያም መክረዋል።

ዶክተር ቴድሮስ በውይይቱ ወቅት በሁለቱ አገራት መካከል ያለው ግንኙነት ወደተጠናከረ የንግድና ኢንቨስትመንት ትብብር መሸጋገር እንዳለበት ተናግረዋል።

የእንግሊዝ ባለሃብቶች በቅርቡ ለስራ ክፍት የሆነውን የሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች እየተገነቡ በሚገኙ ፓርኮች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።

አገሪቱ የጤናውን ዘርፍ ለማጠናከር በትኩረት እየሰራችበት ባለው የፋርማሲቲካል ኢንዱስትሪ ማስፋፋት ላይም የእንግሊዝ ባለሃብቶች ተሳትፎ ይፈለጋል ብለዋል።

ልዑኩን የመሩት በኢትዮጵያ የጠቅላይ ሚኒስትሯ የንግድ ልዩ መልዕክተኛ ሚስተር ሪቻርድ ቤንዮን በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ የጀመረችው የለወጥ ራዕይ እውን እንዲሆን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የነበሩትን የአገሪቱ ኩባንያዎች ከማበረታታት ባሻገር ሌሎችም እንዲመጡ ለማድረግ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የአገራቸው ባለሃብቶች በሰው ሃይል ስልጠናም ሆነ በንግዱ ዘርፍ በቀጥታ በመሳተፍ በኢትዮጵያ እየተስፋፉ በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲገቡ ይደረጋል ብለዋል።

የመሠረተ ልማት ዝርጋታና የኃይል ምንጮች ላይ ኢንቨስት ማድረግ ሌላው የትኩረት መስካቸው መሆኑንም አስታውቀዋል።

የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረው የተማረና የተሻለ ገቢ ያለው ህብረተሰብ የመፍጠር ጥረት እንዲሳካ አገራቸው የተለያዩ ድጋፎችን እንደምታደርግ መናገራቸውንም ተዘግቧል።( ኢዜአ)