የቤተ አባይ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማዕከል ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

ባህዳር፤ ሐምሌ 23/ 2008 (ዋኢማ) -በባህርዳር ከተማ በ390 ሚሊየን ብር የሚገነባው የቤተ አባይ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ማዕከል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

መሰረተ ድንጋዩን ያስቀመጡት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንድአርጋቸው ባሰሙት ንግግር ማዕከሉ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ዓለም የደረሰበትን ደረጃ ለትውልዱ ቀርፆ በማስቀመጥ ረገድ በቀጣይ የሚደረጉ ችግር ፈቺ ጥናቶች የሚካሄዱበት መሆኑን ገልጸዋል ።

ለማዕከሉ ግንባታ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመው፤ የዳያስፖራ አባላቱ ደግሞ በሚኖራቸው ተሳትፎ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ እንደማይጠራሩ አስገንዝበዋል፡፡

የአማራ ተወላጅ ዳያስፖራ በተወካዮቻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሀገራቸው ልማት ላይ ለመሳተፍ የተፈጠረላቸውን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በቴክኖለጂ ኢንፎርሜሽን ሽግግር ላይ የበኩላችን ድርሻ እንደሚወጡ አረጋግጠዋል ፡፡

ማዕከሉ በ20 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍና በዲያስፖራው የራሱን አሻራ ለማሳረፍ ሲባል ሙሉ ወጪው ራሱ የሚሸፈነው መሆኑን በስነ ስርዓቱ ላይ ተመልክቷል፡፡

በ390 ሚሊየን ብር የሚገነባው ይህ ማዕከል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የፈጠራ ስራዎች የሚበለፅጉበትና ሀገሪቱ የያዘችውን የዕድገት ጉዞ የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል።

በሌላ በኩል በ260 ሚሊየን ብር የተቋቋመና በ51 ሄክታር ላይ አበባ፣አትክልትና ፍራፍሬ የሚያመርተው የጣና ፍሎራ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያና እንደዚሁም የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ በዳያስፖራው መጎብኘታቸው ተመልክቷል  ፡፡

በዓሉን ለማድመቅ በባህርዳር ስታድየም የአማራ ክልል አመራሮችና የክልሉ ተወላጅ ዳያስፖራዎች መካከል የእግር ኳስ ውድድር ትናንት ተካሂዷል፡፡

“የዳያስፖራ ተሳትፎ ለህዳሴያችን!” በሚል ቃል ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የዳያስፖራ ቀን ነገ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ሲል ዋልታ ከስፍራው ዘግቧል፡፡