ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን በልማት ተሳትፎ ድርሻቸውን እያበረክቱ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2008(ዋኢማ)-በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን በሀገር ልማት ተሳትፎ የድርሻቸውን እያበረክቱ  መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  አስታወቀ ።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሠጡት መግለጫ በውጭ አገራት ኑሯቸውን ከመሰረቱ ኢትዮጵያውንያንና ትውልድ ኢትዮጵያውን በዚህ ዓመት 4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ አገር ውስጥ መላካቸውን ገልፀዋል ።

ባለፈው ዓመት 6 ሺህ 200 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ከሚኒስቴሩ የተለያዩ መረጃዎች ለመውሰድ መምጣታቸውም የተሳትፎውን ማደግ የሚያሳይ እንደሆነም አስረድተዋል።

በሚኒስቴሩ መረጃ ፍለጋ ከመጡት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን መካከል ከ 3 ሺህ በላይ የሚሆኑት በኢንቨስትመንት ውስጥ ገብተው እንዲንቀሳቀሱ የተለያዩ እገዛ መደረጉን አስረድተዋል።

ባለፉት 11 ወራት 4 ሺህ 500 በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን የባንክ ሂሳብ ከፍተው ከ32 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ በቁጠባ ሂሳብ አስገብተዋል ያሉት ቃለ አቀባዩ በልማቱ ዘርፍ ከመሳተፍ በተጨማሪ በቋሚነት ከአዲስ አበባና ከጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር ተማሪዎችን በማማከር በትምህርት መስክ የበኩላቸውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።

ይህን ተከትሎ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ንግድና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች የሚያደርገው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን አስረድተዋል።በእስካሁኑ ሂደት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን  ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከ 37 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት።

ድጋፉ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውን ከአገራቸው ጋር ያለው ትስስርና ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን የሚያመላክት  መሆኑን ጠቁመው እስካሁን የተከናወኑ የክልልና አገር ዓቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫሎች አገራዊ አመለካከት መቀየር እንዳስቻለ በመግለጫው አመልክተዋል ።( ኢዜአ)