ኢንስቲትዩቱ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 91 በመቶ ዕቅዱን መፈጸሙን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 23/2008(ዋኢማ)- የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት  በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ለማከናወን ከያዘው ዕቅድ  በአማካኝ 91 በመቶ የሚሆነውን  መፈጸሙን  አስታወቀ ።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አዱኛ ዋቅጅራ ለዋልታ እንደገለጹት ተቋሙ በ2008 የበጀት ዓመት አዳዲስ  የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ ፣ መነሻ  ዘሮችን በማውጣት፣ ለአርሶ አደሩ የአቅም ግንባታ ሥልጠናዎች በመሥጠት ረገድ ከያዛቸውን ዕቅዶች ውስጥ  91  በመቶ  የሚሆነውን ማከናወን ችሏል ብለዋል ።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በአጠቃላይ 554 የግብርና ቴክኖሎጂዎችንና አሠራሮች  ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ  ኢንስቲትዩቱ ሲሰራ  መቆየቱን  የገለጹት ዶክተር  አዱኛ  502  የሚሆኑ የተለያዩ ቴክሎጂዎችንናአሠራሮች  ማውጣት መቻሉን ዶክተር አዱኛ ገልጸዋል።

ኢንስቲትዩቱ በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 49 የሚሆኑ የአገዳ ሰብል፣ የብዕር ሰብል፣ የጥራጥሬ ፣ ቅባት እህሎችና የአትክልት ምርጥ  ዝርያዎችን  በማውጣት  ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ መደረጉን  የተናገሩት ዶክተር አዱኛ  49 ዝርያዎቹም ወጥተው  በብሔራዊ  የዝርያ አፅዳቂ ኮሚቴ ተገምግመው ተቀባይነት አግኝተዋል ብለዋል።

በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂና አሠራሮችን እንዲላመዱ ለማስቻል በበጀት ዓመቱ ለ48ሺ 599 አርሶ አደሮች የአቅም ግንባታ ለመሥጠት ታቅዶ 40ሺ 905 የሚደርሱ አርሶ አደሮች በተለያዩ የግብርና ፓኬጆች በማቀፍ   ሥልጠናና ምክረ ሐሳቦች መሥጠቱን ዶክተር  አዱኛ ተናግረዋል ።

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ በአገሪቱ የተከሰተውን የድርቅ ሁኔታ ለመቋቋም ፈጥነው የሚደርሱና ድርቅን የሚቋቋሙ የማሽላ ፣ የማሾና የጤፍ አዳዲስ  ዝርያዎችን  በማውጣት  ለተጠቃሚዎች  እንዲሠራጩ  መደረጉን  ዶክተር አዱኛ አመልክተዋል ።

ኢንስቲትዩቱ ከድርቅ ጋር ተያያዞ  የተከሰተውን የእንስሳት መኖ እጥረት ችግርን ለመቅረፍ ውጤታማ  የሆኑ  የሣር  ዝርያዎችን  በማውጣት  በተለያዩ  የአገሪቱ  ክፍሎች  እንዲባዙ  በማድረግ   የበኩሉን  አስተዋጽኦ ማበርከቱን  ዶክተር  አዱኛ አስረድተዋል ።

የኢትዮጵያ  የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት  በሥሩ  በሚገኙት 17  የግብርና  ምርምር  ማዕከላት  በመጠቀም   ለአገሪቱ  የአየር ሁኔታ  መሬት አቀማመጥና  ብዝሃ ሕይወት ጋር ተስማሚ  የሆኑ  የግብርና ቴክኖሎጂዎችና አሠራሮችን በማቅረብ ላይ ይገኛል ። 