ህብረቱ ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል የ20 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22/2008(ዋኢማ)- የአውሮፓ ኅብረት ህገ-ወጥ ስደትን ከምንጩ ለመከላከልና ለወጣቶች ሥራ ፈጠራ የሚውል የ20 ሚሊዮን ዩሮ ለኢትዮጵያ ድጋፍ አደረገ።

የገንዘብ ድጋፉ ለአራት ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በአገሪቱ የሰሜኑና የመካከለኛው ክፍል የሚደረገውን ህገ-ወጥ ስደት  እንዲቀንስ ታስቦ የተጀመረ ፕሮግራም ነው ተብሏል።

በዚህም በአማራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ክልል የሚኖሩ ወጣቶችን በተለያዩ ሥራዎች ተሳታፊ በማድረግ ለስራ ዕድል ፈጠራ እንደሚውል ነው የተገለፀው።

የአውሮፓ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅትና አለም አቀፍ የሠራተኞች ድርጅት ፕሮግራሙ ተፈፃሚ እንዲሆን ስምምነት ፈጽመዋል።

በኢትዮጵያ የኅብረቱ ተወካይ አምባሳደር ሻንታል ሂብርቻት እንዳሉት ድጋፉ በአገሪቱ ለህገ-ወጥ ስደት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ወጣቶች ኢኮኖሚያቸውን ማሳደግ እንዲችሉ የሥራ ዕድልን የሚፈጥር ነው።

ኢትዮጵያ ከኅብረቱ ጋር በተለያዩ የልማት ጉዳዮች እየሰራች መሆኑን አስታውሰው በአካባቢዋ ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን አምባሳደሯ ተናግረዋል።

የአለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት ተወካይ ቅድስት ጫላ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት ስደት የዓለማችን ሥጋት እየሆነ መጥቷል ብለዋል።

በአገሪቱ በየዓመቱ ከሶስት ሚሊዮን በላይ የሚሆን የሚሰራ ኃይል ወደ ሥራ የሚቀላቀል ቢሆንም በከተማም ሆነ በገጠር ለእነዚህ ወጣቶች የሚፈለገውን ያህል የስራ ዕድል አልተፈጠረም ነው ያሉት።

በእነዚህና በሌሎች ምክንያቶች ወጣቶች ከትውልድ አገራቸው ወጥተው ወደ ሌሎች የዓለም አገራት ይሰደዳሉ ብለዋል።

ለፕሮግራሙ መሳካት ምቹ የስራ አካባቢና የስራ ዕድል እንዲፈጠር ድርጅቱ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል።  

ከሶስት በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለም ህዝብ ከትውልድ ቀዬው በመውጣት በተለያዩ የዓለም አገራት በስደት እንደሚኖር በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015 የተደረገ ጥናት ያሳያል።

በአፍሪካ ደግሞ ከ31 ሚሊዮን በላይ የሚሆነው ህዝብ በአውሮፓ፣ በመካለኛው ምስራቅና እዛው በአፍሪካ የተለያዩ አገራት በስደት እንደሚኖር እና በ2016 ደግሞ ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአፍሪካ ዜጎች የሜዲትራንያን ባህርን በህገ-ወጥ መንገድ አቋርጠው እንተደተጓዙም ጥናቱ ያሳያል።(ኢዜአ)