የባቡር ፕሮጀክቶች በራስ አቅም የመገንባት አቅም እየተፈጠረባቸው ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21/2008 (ዋኢማ)- በሀገሪቱ እየተከናወኑ ያሉ የባቡር ፕሮጀክቶች በቀጣይ በራስ አቅም ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን ለመምራት የሚያስችል አቅም እየተፈጠረባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ኢንጅነር ጌታቸው በትሩ ተናገሩ።

የባቡር መስመሮቹ በአሁኑ ወቅት በውጭ ሀገር የስራ ተቋራጮች እየተገነቡ ቢሆንም፥ ኢትዮጵያውያን የራሳቸውን አሻራ በማሳረፍ በቀጣይ በሀገሪቱ በሚገነቡ የባቡር መስመሮች ላይ በራስ አቅም ለመሳተፍ የሚያስችል ክህሎት እየተፈጠረ መሆኑን ዶክተር ኢንጅነር ጌታቸው በትሩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በመቀሌ-ወልድያ-ሀራ ገበያ የባቡር ግንባታ ላይ ኢትዮጵያውያን በትላልቅ የዋሻ ቁፋሮ ላይ እየተሳተፉ መሆናቸውንም ያነሳሉ።

ፕሮጀክቱ ከ3 ኪሎ ሜትር በላይ የሚረዝሙ ትላለቅ ዋሻዎችን ጨምሮ እስከ 150 ሜትር ከፍታ ያላቸው ድልድዮች ግንባታን ያካተተ ነው።

በእነዚህ ግንባታዎች ሁሉ ኢትዮጵያውያን በመሳተፍ ላይ ናቸው የሚሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ በአብዛኛው የማሽን እና ሌሎች ተዛማች ነገሮች ላይ የኢትዮጵያውያን ተሳትፎ ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል ብለዋል።

አሁንም ግን በእነዚሁ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ላይ በተግባር ስራ ላይ ሙሉ በሙሉ ከመሳተፍም ባለፈ በመጀመርያ ምእራፍ በሚከናወነው በዲዛይን ወይም በንድፍ ስራ መሳተፍ ላይ ክፍተት እንዳለ ያነሳሉ።

ይህን ክፍተት ለመሙላት ደግሞ በዚሁ ፕሮጀክት ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ ዩንቨርሲቲዎች እንዲሳተፉ እያደረግን ነው ብለዋል።

ከእነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በተጨማሪ ግንባታቸው ተጠናቀው ወደ ስራ በገቡት የባቡር መስመሮች ላይ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያንን በማሳደግ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን እንዲመራ የማድረግ ስራውም ውጤት እያመጣ መሆኑን ነው ዶክተር ኢንጅነር ጌታቸው የነገሩን።

ባለፈው አመት አገልግሎት መስጠት በጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ ፕሮጀክት ላይ እየተሳተፉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቁጥር 48 በመቶ ብቻ መሆኑንም ያነሳሉ።

ይህ ቁጥር በሚቀጥሉት ሁለት አመታት ሙሉ ለሙሉ በኢትዮጵያውያን መተካት አለበት ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ ለዚህም የሀገር ወስጥ ተሳትፎን ከፍ በማድረግ የውጭ ሀገር ተሳትፎውን መስከረም ወር ላይ ወደ 27 በመቶ ዝቅ ይደረጋል ብለዋል።

እንዲሁም የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አሽከርካሪነት የተሰማሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ከመጭው መሰከረም ወር ጀመሮ በኢትዮጵያውያን እንደሚተኩም ተነግሯል።

በእዚህ መልኩ አሁን ላይ የተጀመረው የቴክኖሎጂ ሽግግሩ ከቀጠለ፥ በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት የአዲስ አበባውን የባቡር መስመር ሙሉ ለሙሉ በሀገሬው ሰው መምራት እንደሚቻል ያረጋግጣሉ።

በሚቀጥሉተ ሁለት ወራት ወደ ስራ በሚገባው የአዲስ አበባ-መኢሶ-ደዋንሌ የባቡር ፕሮጀክትም የባቡር መስመሩ በውጭ ኩባንያ ለስድስት አመታት ይተዳደራል ያሉ ሲሆን፥ ከዚያ በኋላ መስመሩን ማስተዳደር የኢትዮጵያውያን ሚና ይሆናል ብለዋል።

በዚኛው የማስተዳደር ዘርፍም የኦፕሬቲንግ ወይም መስመሩን በቴክኖሎጂ በመታገዝ የመምራት ስራ ላይ የሚታይ ችግር መኖሩን የሚያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚው፥ ይህን ክፍተት ለመሙላትም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን ነው የነገሩን።

ኢትዮጵያ ካለፉት አምስት ዓመታት ጀምሮ በርካታ ግዙፍ የባቡር ፕሮጀክቶችን በማከናወን ላይ ነች።

ከፕሮጀክቶቹ አንዱ የሆነው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር መስመር አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ከአስር ወራት በላይ ተቆጥሯል።

የአዲስ አበባ መኢሶ ደዋንሌ ባቡር ፕሮጀክትም ግንባታው ከ98 በመቶ በላይ ተጠናቆ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል።

ግንባታው ከ1 ዓመት በፊት የተጀመረው እና በሚቀጥሉት 2 ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቀው የመቀሌ-ወልዲያ-ሀራ ገበያ የባቡር መስመርም አሁን ላይ ከ36 በመቶ በላይ ግንባታው መጠናቀቁን ነው ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው።(ኤፍቢሲ)