ኮርፖሬሽኑ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እንደሚመረቁ አስታወቀ  

በቻይና ኩባንያዎች እየተገነቡ የሚገኙ ሁለት የኢንዱስትሪ ፓርኮች በሚቀጥለው ወር እንደሚመረቁ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

በሚቀጥለው ወር የሚመረቁት ሁለቱ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የመቀሌ እና የኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ናቸው።

የኢንዱስትሪ ፓርኮቹ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት የሚያመርቱ መሆናቸው ነው የተነገረው።

ፓርኮቹ በ250 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ የተገነቡ ናቸው ተብሏል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ በጨርቃ ጨርቅ እና አልባሳት ምርቶች ከፍተኛ አቅም ያላት ሲሆን፥ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 ዘርፉ 1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ የሚያስገኝ መሆኑ ተጠቁሟል።

አራት የኢንዱስትሪ ፓርኮች  እኤአ በ2017 መጨረሻ ይጠናቀቃሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡