የቻይናው ኩባንያ በሶላር ኢነርጂ መስክ በኢትዮጵያ ሥራ ጀመረ

ሽንዜን ለሚ የተባለ የቻይና ኩባንያ በኢትዮጵያ በሶላር ኢነርጂ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ሰራ መጀመሩ ይፋ አደረገ፡፡

ኩባንያዉ በተለያዩ አለም ሀገራት ላይ ምርቶቹን በማቅረብ እዉቅና ያተረፈ ሲሆን በኢትዮጵያ ጥራት ያላቸዉ ምርቶች ለህብረተሰቡ እንደሚያቀርብ አስታቋል፡፡

ኩባንያዉ እንደገለጸዉ የተጠቃሚዉ አቅም ባገናዘበ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸዉ ምርቶችን ለህብረተሰቡ በማቅረብ ሀገሪቱ ከያዛቸዉ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እቅድ የሚያግዝ ስራዎችን እንደሚሰራ ገልጿል፡፡

በመላዉ የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ግለሰቦች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ ሀገር በቀል ባሀብቶች ጋር በመተባበር እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

የቻይና ኩባንያ ዋና ማእከሉ በኢትዮጵያ በማድረግ ለዘርፉ የሚያግዝም ማርቶች በማምረት ለጎረቤት ሀገራት የማቅረብ እቅድ እንዳለዉ ተጠቅሷል፡፡