እነ አቶ መላኩ ፈንታ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 12 / 2006 (ዋኢማ) -አቶ መላኩ ፈንታ፣ አቶ ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስና ሌሎች 31 ሰዎች የተካተቱበት የክስ መዝገብ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረበ።

 

ተጠርጣሪዎቹ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው ክሱ ተነቦላቸዋል።

 

በዚህ መዝገብ የፌደራል የስነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ሀግ 28 ክሶችን ነው የመሰረተው።

 

የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ በጥቅሉ 138 ክሶችን በተጠርጣሪዎቹ ላይ የመሰረተ ሲሆን፥ ክሶቹ በሶስት የተለያዩ መዝገቦች ቀርበዋል።
በዛሬው ችሎት ከክስ መዝገቡ ጋር የሰነድ ማስረጃን አቃቤ ሀግ ያላቀረበ ሲሆን ፥ የተጠርጣሪ ጠበቆች በክረምት ውስጥ ለተመነሰረተ ክስ የሰነድ ማስረጃ ዛሬ አልቀረበም ማለት ተገቢ ስላልሆነ አቃቤ ህግ የሰነድ ማስረጃዎቹን ዛሬ ለፍርድ ቤቱ ሊያቀርብ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል።

 

ፍርድ ቤቱም ከጠበቆቹና ከአቃቤ ህግ የቀረበውን ክርክር ሰምቶ ብይን ለመስጠት መጀመሪያ ሙሉ ክሱን ማንበብ እንዳለበት ተናግሯል።
ችሎቱ ሰኞ ከሰአት በኋላ ውሎው ክሱን በንባብ አሰምቷል፥ የቀረበውንም ክርክር ላይ ነገ ብይን እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
ችሎቱ 93 እና 17 ክሶች የተካተቱባቸውን ሁለት የክስ መዝገቦች ለነገ ከሚሰጠው ትእዛዝ ጋር አንድ ላይ ለመመልከት በይደር ቀጠሮ ይዟል።(ኤፍ ቢ ሲ)