26 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የኤሌክትሪክ አውቶብሶች አገልግሎት መስጠት ጀመሩ

መጋቢት 16/2016 (አዲስ ዋልታ) 26 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የመጀመሪያዎቹ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች በአዲስ አበባ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡

ዛሬ ስራ የጀመሩት 60 አውቶቢሶች በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ እህት ድርጅት ቬሎሲቲ ኤክስፕሬስ በገላን እና ደብረ ብርሃን የተገጣጠሙ መሆናቸውን ድርጅቱ ገልጿል፡፡

አውቶብሶቹ ቻርጅ የሚደረጉበት ስፍራ በ30 የተለያዩ የከተማዋ ስፍራዎች መገንባታቸውንና በቤት ውስጥ ቻርጅ መደረግ እንደሚችሉም ተገልጿል፡፡

የአውቶብሶቹ መነሻ ቦሌ ሲሆን መዳረሻቸው በእስጢፋኖስ አራት ኪሎ – ስድስት ኪሎ – ሽሮ ሜዳ መሆኑንም ድርጅቱ አስታውቋል።

በበላይነህ ክንዴ ግሩፕ የተገጣጠሙ ተሽከርካሪዎች ብዛት እስካሁን ከ216 በላይ መድረሳቸውንም ድርጅቱ ለአዲስ ዋልታ ዲጂታል ሚዲያ አስታውቋል፡፡

በየኔወርቅ መኮንን