ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች በድንች ተክል ህይወታቸውን እየለወጡ ነው፡ ዘ ጋርዲያን

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 7/2006 (ዋኢማ) – የደሴ ዙርያ ወረዳ አርሶ አደሮች ለዘመናት የአካባቢው መልከአምድራዊ አቀማመጥ አስቸጋሪ ከመሆኑ የተነሳና የአፈር ለምነቱ ለአዝርዕት የማይመች እንዲሁም ከፍተኛ የአፈር መከላት የነበረነበት አካባቢ በመሆኑ ዜጎች ለችግር የተገላጡ ነበሩ  ሲል የእንግሊዙ ዘጋረዲያን ጋዜጣ አትቷል፡፡

በዚህ የተነሳ በአከባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች  ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ሊገፉ ተገደው ነበር፡፡ እንዲያውም አንዳንድ አርሶ አደሮች ያላቸውን ትንሽ ጥሪት ሽጠው ወደ ከተማ የቀን ስራ ለመስራት ለመሄድ እየተዘጋጁ ባሉበት ቅፅበት የድንች ተክልን እንዲተክሉ በተዘረጋው ፕሮጀክት ህይዎታቸውን እየቀየሩ ይገኛሉ ይላል የዘጋርዲያን ዘገባ፡፡

በድንች ተክልም በበዙ ሺህ የሚቆጠር ገንዘብ ወደ ኪሳቸው በማስገባት ከእጅ ወደ አፍ የነበረው ህይዎታቸውን ቀይርው የተንደላቀቀ ህይዎት እይገፉ ይገኛሉ፡፡

በፕሮከጅቱ እስካሁን ድረስ 10ሺ ዜጎች ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን የወረዳው አስተዳደር በቀጣይ 7ሺ አርሶ አደሮችን የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደታሰበ ተናግሯል፡፡

ከዚህ ቀደም አርሶ አደሮች ከ1 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ 75 ኪሎግራም ገብስ ብቻ እንደሚያገኙ የገለጸው የዘጋርዲያን ዘገባ በአሁኑ ሰዓት ግን በተመሳሳይ የሄክታር ሰፋት ላይ 20 ኩንታል ድንች እያገኙ አንዱን ኩንታል ድንች  በ340 ብር በመሸጥ ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውን ያትታል ሲለ ዘ ጋረዲያንን ጠቅሶ ኢሬቴድ ዘግቧል።