የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ 50 በመቶ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 13 / 2006 (ዋኢማ) ¬- የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ግንባታ 50 በመቶ ተጠናቀቀ።
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ግንባታውን አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አንዳስታወቀው የመሬት ውስጥ የዋሻ ስራዎችና ድልድዮች ግንባታ በተገቢው ሁኔታ ተከናውነዋል ፤ ሀዲድ የማንጠፍ ስራውም ከ6 ኪ.ሜ በላይ ደርሷል።
ከኤሌትሪክ ፣ ከውሃና ከስልክ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ተጓዳኝ ጥያቄዎችን ለመመለስም እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ከወሰን ማስከበር ጋር በተያያዘ ይነሱ የነበሩ ችግሮችንም ከሞላ ጎደል መቅረፍ  መቻሉን  የኮርፖሬሽኑ ህዝብ ግንኝነት ሃላፊ አቶ አበበ ምህረቱ ተናግረዋል። (ኤፍ.ቢ.ሲ.)