ጥልቅ ተሃድሶው ተጠናክሮ መቀጠሉን መንግስት አስታወቀ

ለህዳሴው ጉዞው ውስጣዊ እንቅፋት የሆነውን ችግር ለመቅረፍ ጥልቅ ተሃድሶው ተጠናክሮ መቀጠሉን መንግስት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት በሳምንታዊ የአቋም መግለጫው እንዳለው መንግስት በጥልቀት የመታደስ እንቅስቃሴውን ደረጃ በደረጃ እያሰፋና ትርጉም ወዳለው ደረጃ ከፍ እያደረገ ይገኛል፡፡

የፌዴራል መንግስት አዲሱ ካቢኔም ሃላፊነቱን ተረክቦ ስራውን መጀመሩን ገልጿል፡፡

ክልላዊ ብሔራዊ መንግስታትም ተመሳሳይ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆናቸውንም እንዲሁ፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግርን የሚፈታ፣ ህዝብ አገልጋይ መዋቅር ዳግም ለመፍጠር ይጥራልም ብሏል፡፡

ህብረተሰቡም ከመንግስት ጐን በመቆም የሚያሣዩትን አጋርነት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡(ኢቢኮ)