የትግራይና አማራ ክልሎች ህዝብ የጋራ ምክክር መድረክ በዛሬው ዕለት በጎንደር ከተማ መካሄድ ጀመረ ።
በምክክረ መድረኩ ላይ የሚሳተፉት 500 የሚደርሱ የትግራይ ክልል ምሁራን ፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ወጣቶችና አመራሮች በትናንትናው ዕለት ምሽት ወደ ጎንደር ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባባል ተደርጎላቸዋል ።
በዘሬው ዕለት በጎንደር ከተማ በተጀመረው የምክክር መድረክ በሁለቱ ክልሎች ህዝቦች መካከል ተከስቶ የነበረውን አለመግባባት በዘላቂነት መፍታት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት እያደረጉ መሆኑ ይገኛሉ ።
የሁለቱ ክልሎች ተወካዮች ሰላምና የልማት ሂደትን በሚያረጋግጡባቸው የጋራ ጉዳዮች ላይም ምክክር ያካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
በትግራይና አማራ ክልል ሕዝቦች መካከል ያለመግባባትና ቅራኔ ባለፈው ዓመት መከሰቱ ይታወሳል ።
የሁለቱ ክልሎች ህዝቦች ባለፈው ዓመት ነሓሴ ወር መቐለ ከተማ ላይ የጋራ ምክክር ማካሄዳቸው ይታወሳል ።