የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አልጋወራሽ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን በኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።

አልጋወራሹ በቆይታቸው ወቅት ከኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በጋራ ጉዳዮች እና አካባቢያዊ ሁኔታዎች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳፋኪ መሐማት ጋርም እንደሚወያዩ የሚጠበቅ ሲሆ የመስክ ጉብኝትም እንደሚያደርጉ ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በቅርቡ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል።

የሀገሪቱ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለንዋያቸውን በተለያዩ መስኮች ያፈሰሱ ሲሆን በቀጣይም በግብርናና ቱሪዝም መስኮች እንደሚሰማሩ ይጠበቃል።