አልማ በደብረብርሃንና አካባቢው ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር/አልማ/ በደብረ ብርሃንና አካባቢው ከሚገኙት አባላቱ ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ ።

በደብረ ብርሃን አካባቢ የአልማ ቅርንጫፍ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰለሞን ጉታ ለዋልታ እንደገለጹት በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን አካባቢ ህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያደርጉ የልማት ሥራዎችን ለማከናወን ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቧል ።

የአማራ ህዝብንና አጋር አካላትን በማሳተፍ በደብረ ብርሃን አካባቢ የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በየዓመቱ የአልማ አባላትን ቁጥር በ14 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን አቶ ሰለሞን ተናግረዋል ።

እንደ አቶ ሰለሞን ገለጻ አልማ በአማራ ክልል የሚገኙ አባላቱንና ደጋፊዎች በማሳተፍ  በክልሉ  የሚገኙ  የማህበራዊ  ችግሮችን  ለመፍታት  የሰነቃቸውን ራዕይ  ለማሳካት  እየተንቀሳቀሰ ነው    

በጉኤውም  በድብረብርሃንና አካባቢው አልማ ያከናወናቸው የትምህርት ፣ ጤና ፣ የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራና ሙያ ክህሎት ሥልጠና ላይ የሚታዩ ችግሮችን የሚለዩበትና ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል አቶ ሰለሞን ።     

አልማ  በዘንድሮ  ዓመት የቅርንጫፍና መሠረታዊ ማህበር ጉባኤው  የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን   ፈጥኖ በማጠናቀቅ የአባላትን ፍላጎትና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጡ ጉዳዮች ላይ  እንደሚመክር  ተገልጿል ።