301 ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረቢያ ተመለሱ

መጋቢት 29/2013 (ዋልታ) – 301 ኢትዮጵያዊያን በዛሬው ዕለት ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ ከተማ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

ለተመላሾቹ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ከሚኒስቴሩ ቃልአቀባይ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡