ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር አብይ አህመድ ወደ ፈረንሳይ አቀኑ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአውሮፓ  በፈረንሳይና  ጀርመን ይፋዊ የሥራ ጉበኝት ለማድረግ በዛሬው ዕለት  ወደ ፓሪስ አቅንተዋል  ።

ጠቅላይ  ሚንስትሩ በፈረንሳይ በሚኖራቸው ቆይታም ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር በፓሪስ ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።

በመቀጠልም ወደ ጀርመን የሚያቀኑ ሲሆን በዚያም ከመራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚወያዩ ይሆናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በጀርመን ቆይታቸውም ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ከሚውጣጡ 25 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ጋር በፍራንክፈርት ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአውሮፓ ጉብኝት “አንድ ሆነን እንነሳ ነገን በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ መሆኑም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን የሚያደርጉትቀደም ሲል  በሀገራቱ መሪዎች በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ነው።