ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በአፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ደቡብ አፍሪካ አቀኑ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ  ዘውዴ  በአፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ለመካፈል በዛሬው  ዕለት  ወደ ደቡብ አፍሪካ አቀኑ ።

በደቡብ አፍሪካ  በሚካሄደው የአፍሪካ ኢንቨስትመንት ፎረም  ላይ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት፣ ኢንቨስተሮች እና ሌሎች ሌሎች ተቀማት ይገኛሉ ተብሏል ።

የኢንቨስትመንት ፎረሙ በአህጉሪቱ  የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ይበልጥ  በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንቱ እንዲስፋፋ የበኩሉን ሚና እንደሚጫወት  የሚጠበቅ ሲሆን፥ ኢትዮጵያም ያላትን የኢንቨስትመንት ዕድል ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለመጡ ተሳታፊዎች  ለማስተዋወቅ ተዘጋጅታለች ።

የአፍሪካ አንቨስትመንት ፎረም ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ  የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት በመሆን ከተሾሙ በኋላ  ለሁለተኛ ጊዜ የሚያደርጉት የውጭ ሀገር ጉዞ ነው።