የአምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ የቀብር ሥነ-ሥርዓት የፊታችን እሁድ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈጸማል

የቀድሞው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ-ጉባኤ የአምባሳደር ዳዊት ዮሐንስ

የቀብር ስነ-ስርዓት እሁድ ጥር 26 2011 ዓ.ም በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተክረስቲያን እንደሚፈጸም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ለአምባሳደር ዳዊት ዮሀንስ አስክሬን ዛሬ በኒዮርክ ከተማ ሸኝት የሚደረግለት ሲሆን አስከሬኑ ነገ ጥር 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ከምሽቱ 3፡30  በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል፡፡

ለአስከሬኑ በከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ በቤተሰቦቻቸው እና በወዳጆቻቸው  አቀባበል ከተደረገ በኋላ በፖሊስ በክብር ታጅቦ ወደ መኖሪያ ቤታቸው እንደሚጓዝ ምክር ቤቱ የላከልን መረጃ ያመለክታል፡፡