ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ሸንጎ መሪ ጋር በስልክ ተወያዩ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ሸንጎ መሪ ሌተና ጀነራል አብዱል ፈታሕ አል-ቡርሀን ጋር በስልክ ተወያዩ።

ሁለቱ ወገኖች በሱዳን ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት ስለተጀመረው ሽምግልና ሂደት ዙሪያ በስልክ መወያየታቸወን ነው የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያስታወቀው።

በውይይታቸው ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች እንዴት ይቀጥሉ በሚለው ላይ ትኩረት ማድርጋቸውም ነው የተመለከተው።

አሁን ያለው ሁኔታ የተሻለ መፍትሄ እንደሚያገኝ ተስፋ እንዳላቸውም ሁለቱ ወገኖች አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ባለፈው አርብ ወደ ሱዳን በማቅናት ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ሸንጎ መሪ ሌተና ጀነራል አብዱል ፈታሕ አል-ቡርሀን ጋር መወያየታቸው ይታወሳል።