የአለም ባንክ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትብብርን ለማጎልበት የሚያስችል ፕሮጄክት ይፋ አደረገ

የአለም ባንክ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ ትብብርን ለማጎልበት የሚያስችል የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ማጎልበትና ቀጠናዊ ትስስር ፕሮጄክት ይፋ አድርጓል፡፡

በፕሮጄክቱ ኢትዮጵያ፣ ታንዛኒያ እና ኬንያ የተካተቱ ሲሆን የአለም ባንክ የ3ቱ ሃገራት ተወካዮች በተገኙበት ነው ፕሮጀክቱን ይፋ ያደረገው፡፡

ይህ ፕሮጀክት በትራንስፖርት፣ ኢነርጂ፣ ማኑፋክቸሪንግ እና አይሲቲ የሙያ መስኮች ላይ ድጋፍ እንደሚያደርግ የከፍተኛ ትምህርት እና ሳይንስ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብዲዋሳ አብዱላሂ ፕሮጀክቱ ይፋ በተደረገበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በቀጣዮቹ ስድስት ዓመታት 16 የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ወደ የልህቀት ማዕከልነት የማሳደግ እቅድ ይዞ እንደሚሰራም ሚኒስትሩ ተናረዋል፡፡

በተጨማሪም በዚህ ፕሮጀክት በየአመቱ 20 ሺህ ዜጎች መደበኛ እና አጫጭር ስልጠናዎችን እንደሚያገኙ ተጠቁሟል፡፡

የፕሮጀክት ስምምነቱ የተፈረመው በአውሮፓዊያኑ የዘመን ቀመር በ2018 ቢሆንም ተግባራዊነቱ ይፋ የሆነው ዛሬው መሆኑ ታውቋል፡፡