አዲሱ የስደተኞች አዋጅ ስደተኞችንና የተጠለሉበትን ሀገር የሚጠቅም መሆኑ ተገለጸ

አዲሱ የስደተኞች አዋጅ ስደተኞችንና የተጠለሉበትን ሀገር የሚጠቅም መሆኑ ተገለጸ

አዲሱ የስደተኞች አዋጅ  ስደተኞች በካምፕ ተቀምጠው ተረጂ ከሚሆኑ ይልቅ ራሳቸውን ጠቅመው የተጠለሉባትን አገርም ባላቸውእውቀትና አቅም እንዲጠቅሙ እንደሚረዳ ተገለጸ

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ በአዲስ መልክ መቋቋምን አስመልክቶ ዛሬ የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ከበደ ጫኔ በሰጡት መግለጫ፤ የኤጀንሲው በአዲስ መልክ መቋቋም በተለይ በቅርቡ የፀደቀውን የስደተኞች አዋጅ ተድባራዊ ለማድረግ ይረዳል ብለዋል።

ኤጀንሲው በአዲስ መልክ መቋቋም በቅርቡ የፀደቀውን የስደተኞች አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በአዲሱ የስደተኞች አዋጅ ስደተኞች በካምፕ ተቀምጠው ተረጂ ከሚሆኑ ይልቅ ራሳቸውን ጠቅመው የተጠለሉባትን አገርም ባላቸውእውቀትና አቅም እንዲጠቅሙ ያደርጋል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከ9 መቶ 50 ሺህ በላይ ስደተኞችን ተቀብላ በ27 የስደተኞች ካምፕ አስጠልላ ልትገኛለች።

ከነዚህ ስደተኞች 95 በመቶ የሚሆኑት ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንደሆኑም መረጃዎች ያመላክታሉ።

ዳይሬክተሩ አቶ ከበደ ጫኔ ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ ለስደተኞች አስፈላጊውን መብት ለመስጠት መፈረሟንና ይህንም ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራች መሆኑን ጠቁመው፤  ለዚህም በቅርብ የፀደቀው የስደተኞች አዋጅ አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል

ከስደት ተመላሽ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ላይም እየተሰራ ያለ ስራ እንዳለም ዳይሬክተሩ ጠቅሰው፤ በተለይ ተመላሽ ስደተኞች  ወደ ሀገር ከገቡ በኋላ እንዲደራጁ የማድረግ ስራ ከክልሎች ጋር ኤጀንሲው እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡