ጋቦን የነዳጅ ጥገኝነቷን እንደምትቀንስ አስታወቀች

ጋቦን ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ 642 ሚልየን ዶላር ብድር ስታገኝ የነዳጅ ጥገኝነቷን እንደምትቀንስ አስታወቀች፡፡

ማዕከላዊ አፍሪካቷ ሀገር ጋቦን ትንሿ የነዳድ አምራችና ላኪ ሃገራት ማህበር( ኦፔክ) አባል ናት፡፡

በቀን ከ200 000 በርሚል በላይ ነዳጅ ታመርታለች፡፡

30 በመቶው የሃገሪቷ አጠቃላይ ምጣኔ ሃብታዊ ገቢ መሰረቱ ነዳጅ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በተለያዩ ጊዜያት ባጋጠመው የነዳጅ ዋጋ ማሽቆልቆል ምክንያት እንኳን በተለይም በፈረንጆቹ በ2015 3.9 የነበረው የሃገሪቷ ምጣኔ ሃብት በ2016 ወደ ሁለት ነጥብ አንድ መቀነሱን የብሉምበርግ ዘገባ ያሳያል፡፡

ሃገሪቷ በአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ቃል የተገባላትን 642 ሚልየን የአሜሪካን ዶላር ብድር ስታገኝ የነዳጅ አቅርቦት መጠኗን በመቀነስ ፊቷን ወደ ግብርና እና የመአድን ስራ እንደምታዞር የሃገሪቱ የምጣኔ ሃብት ሚኒስቴር ረጊስ ኢሞንጉልት ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ እንዳሉት ከሆነ ጋቦን ብድሩን ስታገኝ አሁን ያለውን 30 በመቶ የነዳጅ ገቢዋን በ2020 አጋማሽ ወደ 25 በመቶ ዝቅ ታደርገዋለች፡፡

ድጎማዎችን በመቀነስ እና የውጭ ኢንቨስተሮችን የሚያሳትፍ የንግድ ሁኔታን በመፍጠር, ምጣኔ ሃብታዊ እድገቷ ወደ 5 በመቶ ሊደርስ ይችላል ተብሏል ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ በፈረንጆቹ ከ2013 ወደዚህ የመጀመርያው ትልቁ ስኬቷ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ብድሩን ያፀደቀው ባለፈው ሳምንት እንደሆነ ያወሳው የብሉምበርግ ዘገባ ጋቦን በፈረነረጆቹ በ1995 ከነዳድ አምራችና ላኪ ሃገራት ማህበር( ኦፔክ) ራሷን አግልላ እንደነበረችና በ2016 በድጋሚ አባል እንደሆነች አስታውሷል፡፡

የማዕከላዊ አፍሪካቷ ሀገር ባለፈው ዓመት ከኦላም ኢንተርናሽናል ኃ.የተ.ሲ. ጋር በመተባበር የወይራ ዘይት እና የጫማ ምርቷን ትልክ እንደነበረም ተጠቅሷል፡፡