የናይጄሪያ ኢንቨስተሮች ከ135 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የግብርና ምርት ግብይት ላይ ሊሠማሩ ነው

ናይጄሪያዊያን ኢንቬስተሮች ከአንድ መቶ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ በሆነ መዋዕለ ነዋይ በግብርና ምርት ግብይት ላይ ለመሰማራት እየተዘጋጁ ነው፡፡

ኢንቬስተሮቹ በካካዋ፣ የፓልም ዘይት፣ ጣውላና ካዛቫ ምርቶች  ላይ በስፋት እንደሚሰማሩም ተገልጿል፡፡

ናይጄሪያኑ ለሃገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የግብርና ምርት ግብይት ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅታችውን አጠናቀዋል፡፡

በህዝብ ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚ የሆነችው ናይጄሪያ በከፍተኛ ሁኔታ በነደጅ ምርቷ ላይ ጥገኛ በመሆንዋ ለዚህ ዘርፍ ትኩረት ነፍጋው ቆይታለች፡፡

የናይጀሪያ መንግስት ችላ ባለው በዚህ  የግብርና ምርት ግብይት ላይ መሰማራቱ ትርፋማ ከማድረጉም ባሻገር ለዘመናት በነዳጅ ምርት ላይ ብቻ ጥገኛ ሆና ለቆየችው ሃገር ተጨማሪ ሃይል እንደሚሆናትም በኢንቬስተሮቹ  ታምኖበታል፡፡

የተቀናጀ የምርት ከተማ ሃላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ማህበር የሚል ሲያሜ የተሰጠው ይህ እንቅስቃሴ ከመዲናዋ ሌጎስ 300 ኪሎ ሜትሮችን ርቆ ይገኛል፡፡

ይህ የንግድ ማሕበር በናይጄሪያ በስፋት በሚመረቱ የካካዋ፣ ፓልም ዘይት፣ ጣውላና የካዛባ ምርት ላይ እንደሚሰማራ ነው የተነገረው፡፡

የሃገሪቱ አርሶ አደሮች ምርቱን በብዛትና በጥራት ማምረት እንዲችሉ ለማበረታታት በማሰብ ማህበሩ በነዚህ ምርቶች ጠቅላላ ንግድ ላይ ሊሰማራ ማሰቡን የማህበሩ ሊቀመንበር ፓት ኡቶሚ ተናግረዋል፡፡

የናይጄሪያ አርሶ አደሮች ከምርቶቻቸው ማግኘት ከሚገባቸው ገቢ ውስጥ 80 ከመቶ ያህሉን እንደማያገኙ ሚስተር ኡቶሚ አስረድተዋል፡፡

ናይጄሪያ ዝቅተኛ የምርት መጠን ለውጭ ገበያ የምትልክ ሃገር ስትሆን የምግብ ምርቶችን ወደ ሃገሯ ለማስገባት ደግሞ ረብጣ ዶላሮችን የምታፈስ ሃገር ነች፡፡

ኢንቬስተሮቿ በግብርና ምርት ግብይት ላይ መሰማራታቸው ቢያንስ ለዓለም ገበያ የምታቀርበውን የምርት መጠን በከፍትኛ ሁኔታ ያሳድገዋል ነው የተባለው፡፡

ናይጄሪያ በካካዋ ምርት ከአፍሪካ አራተኛ ከዓለም ደግሞ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ በፈረንጆቹ 2015/2016 190 ሺህ ሜትሪክ ቶን ካካዋ ለአለም ገበያ አቅርባለች፡፡( ምንጭ: ብሉምበርግ)