በደቡብ ሱዳን ጦርነትን ለማስቀረት የሚያስችል ዕቅድ ተዘጋጀ

የደቡብ ሱዳን መንግስት በሃገሪቱ እና በቀጠናው እየተከሰተ ያለውን ጦርነት ለማስቀረት የሚያስችል አዲስ እቅድ ማዘጋጅቱን አስታወቀ፡፡

በአሁኑ ወቅት ሱዳን በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እየተከሰተ ያለውን ጦርነት ለማስቀረትና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን 3 የተለያዩ ስልቶችን ቀይሳ እየሰራች እንደምትገኝ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ጄኔራል ሳልቫኪር የደህንነት አማካሪ አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ሰአት በአፍሪቃ በተለይም በምስራቅ አፍሪቃ ከፍተኛ ጦርነቶች እና አለመርጋጋቶች ይስተዋላሉ፡፡በተለይም በእርስ በእርስ ጦርነት በምትታመሰው ሱዳን እና በሶማሊያ ጦርነቱ  የከፍ ስጋት ሆኖ ቀጥሏል፡፡በዚህም የተነሳ ብዙ የአህጉሪቱ ዜጎች  ለሞት ከመዳረጋቸውም በላይ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ከመኖሪያ ቀዬአቸው ለመፈናቀል ተገደዋል፡፡

በቅርቡም በሶማሊያማ ሞቃዲሾ በአንድ ከባድ ተሸከርካሪ ላይ በተጠመደ የቦንብ ፍንዳታ ምክንያት  ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሀገሪቱ ዜጎች ለህልፈተ ህይወት መዳረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ በነዳጅ ሀብቷ የበለጸገችው ሱዳንም ረጅም አመታትን ያስቆጠረ የእርስ በርሰ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች፡፡

የደቡብ ሱዳን መንግስት በቅርቡ እንዳስታወቀውም በቀጠናው ሀገራት ላይ የተጋረጠውን የጦርነት ስጋትና የሰላም እጦት ወደ ተረረጋጋ ሁኔታ ለመመመለስ የሚያስችል እቅድ አውጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስተውቋል፡፡

የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት የደህንነት አማካሪ የሆኑት አቶ ቱት ኬው ጋትሉዋክ ለሱዳን ትሪቡን እንደተናገሩት ሀገሪቱ  በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እየተከሰተ ያለውን ጦርነት ለማስቀረትና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን 3 የተለያዩ ስልቶችን ቀይሳ እየሰራች ትገኛለች፡፡

እነዚህ ስልቶችም መንግስታት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ስምምነትን እንዲፈጥሩ  ፤ በሰላም ስምምነቱ  መልሶ ማቋቋም ሂደቶች ውስጥ እንዲሳተፉና የእርስ በርስ ግጭትን ለማስቆም  ከታጣቂ ሀይሎች ጋር  ድርድር ላይ እንዲደርሱ  የሚጠቁም ነው፡፡

በዚህም የሱዳን መንግስት በሀገሪቱ የተከሰተውን የእርሰ በእርስ ግጭት ለማስቆም ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሰላም ስምምነት ለማደስ ፤ በሰላም ስምምነቱ  መልሶ ማቋቋም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ   እና የእርስ በርስ ግጭቱን ለማቆም  ከታጣቂ ሀይሎች ጋር  ለመደራደር መወሰኑን የፕሬዝዳንቱ የደህንነት አማሪ ገልጸዋል፡፡

የፕሬዝዳንቱ አማካሪ እንደገለጹት እነዚህ ስልቶች  በሃገሪቱ እና በቀጠናው እየተከሰተ ያለውን ጦርነት ለማስቀረት መንግስት እየተከተለ ያለውን  ቁርጠኛ አቋም ከማሳየቱም በላይ በቀጠናው እየተከሰቱ ያሉ ጦርነቶችን ለማስቀረት ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

የሱዳን መንግሥት በሀገሪቱ የተፈጠረውን ጦርነት ለማስቆም በትጋት እየሰራ ሲሆን ፕሬዚዳንት ጄኔራል ሳልቫኪርም  ከምክትሎቻቸው  እና ከሌሎች የካቢኔ አባላትና አማካሪዎቻቸው  ጋር በጉዳዩ ላይ በመምከር ላይ ናቸው፡፡

እነዚህ ምክክሮች  ከዚህ ቀደም በኡጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩሪ ሙሴቬኒ የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ አባላት የአሹራ ስምምነትን እንዲፈርሙ ለማደራደር ያደረጉትን ጥረት ፤  የምስራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት  ያካሄደውን  የተሓድሶ ፎረም  እና በናሽናል ዲያሎግ ኢኒሼቲቭ የተከናወኑ የተነሳሽነት ስራዎችን ለመገምገም ዓላማ አድርጎ የተካሄደ መሆኑን  አቶ ቱት ኬው አክለው ገልጸዋል፡፡

እነዚህ አዲስ ስልቶች የሀገሪቱ መንግስት እና የቀጠናው ሀገራት መሪዎች እንዴት ጦርነትን ማስቀርት እንደሚቻሉ የጋራ መግባባት ላይ ለመድርስ የሚያስችል ሲሆን  በተጨማሪም መንግስታት የራሳቸውን የተቀናጁ የፍትህ ስራዎች እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው ይጠቁማል፡፡  

 

የመንግሥትን ቁርጠኝነት ለማሳየት ፕሬዚዳንቱ ብሄራዊ ኮሚቴውን እንደገና ለማደራጀት እና ኮሚቴው ሙሉ ነፃነትን ተቀዳጅቶ የማደራጀት ስራውን እንዲያከናውን  ወስነዋል፡፡  ፕሬዚዳንቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ በመጓዝ ከተቀናቃኛቸው ሬክ ማቻር ጋር በጉዳዩ ላይ ለመመካከር ያደረጉት ጥረት  አልተሳካላቸውም ፡፡

የኮሚቴው አባላት ግን በሱዳን ካርቱም፤ በኬንያ ናይሮቢ እና በኢትዮጵያ አዲሰ አበባ የሚገኙ ተቃዋሚዎችን በማግኘት በጉዳዩ ላይ ምክክር ማድረጋቸውን የፕሬዝዳንቱ አማካሪ  አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡፡፡

ጦርነቱን ለማስቆም እነዚህን ስልቶች የነደፈችው ሱዳን በቅርቡ በተባበሩት መንግስታት የአሜሪካ  ቋሚ ተወካይ  የሆኑት ኒኪ ሀሊን ጉብኝት ታስተናግዳልች፡፡

ተወካዩ በጉብኝታቸው  ፕሬዚዳንት  ሳልቫኪርን ጨምሮ ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለ ስልጣናት ጋር ውይይት እንደሚደርጉ ይጠበቃል ሲል ሱዳን ተሪቡን ዘግቧል፡፡