የአፍሪካን ልማት ለማረጋገጥ ተራማጅ ፖሊሲዎች እንዲተገበሩ ባን ኪሙን አሳሰቡ

የበለፀገች አፍሪካን ለመፍጠርና በሀብቷ ተጠቃሚ እንድትሆን የሚያሰሩ ተራማጅ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጅዎችን መንደፍ እንደሚገባ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ ባን ኪሙን አሳሰቡ፡፡

ባን ኪሙን በአፍሪካ የኢንዱስትሪ ቀን አከባብር ላይ ባደረጉት ንግግር የግሉን ዘርፍ እና የፈጠራ ስራዎችን በማጎልበት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

ሴቶችንና ወጣቶችን በማበረታታት የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማጠናከር እንደሚገባም በአፅንዖት ገልፀዋል፡፡

ይህም እአአ በ2063 የበለፀገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ የተቀመጠውን ዕቅድ ለማሳካት ያግዛል ተብሏል፡፡

እንደ ዋና ፀሃፊው ገለፃ የአፍሪካ ሀገራት ምቹና አስተማማኝ የልማት ማዕቀፍ በመቅረፅ ለለውጥና ዕድገት መንቀሳቀስ አለባቸው፡፡የአፍሪካ ሀገራት ትስስራቸውን በማጠናከር በዓለም ኢኮኖሚ ውስጥ ተሳትፎአቸውን ማሳደግ ይኖርባቸዋል፡፡

እ.አ.አ በ2063 የበለጸገች አፍሪካን ለመፍጠር የአፍሪካ ህብረት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ይታወቃል፡፡