ኡጋንዳና ታንዛኒያ የተደጋጋሚ ፍተሻን ለማስቀረት የጋራ ጣቢያ ሊገነቡ ነው

ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ  በሁለቱም ሀገራት ድንበር ውስጥ ሲደረግ የነበረን ተደጋጋሚ  ፍተሻ ለማስቀረት የሚያስችል የጋራ የድንበር ላይ ፍተሻ ጣቢያ ሊገነቡ መሆኑ  ተገለጸ ፡፡

የጋራ የፍተሻ ጣቢያውን ለመገንባት አስራ ሁለት ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጭ እንደሚጠይቅም ታውቋል፡፡

የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዮሬ ሙሰቬኒ እና የታንዛኒያው አቻቸው ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ ይሁንታን ያገኘው የሀገራቱን ግንኙነት የበለጠውን ያጠናክራል የተባለው ስምምነት በኡጋንዳ ካምፓላ ጉብኝት ሲያደርጉ የቆዩት ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ ውጤት ነው፡፡

የጋራ ፍተሻ ጣቢያው ሁለቱ ሀገራት በሚዋሰኑበት ሙቱኩላ በተባለ ስፍራ ላይ ነው ይገነባል የተባለው፡፡

ለፕሮጀክቱ ፍጻሜ 12 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ተመድቧል፡፡ አንድ ስፍራ ላይ ብቻ ለፍተሻ  እንዲቆም ለማድረግ የሚያስችለው የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ከዚህ በፊት በሁለቱ ሀገራት ውስጥ ሲደረግ የነበረን ፍተሻ በማስቀረት የንግድ ልውውጣቸው ፈጣንና ወጭ ቆጣቢ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የእንግሊዝ እና ካናዳ  አለም አቀፍ የልማት ድርጅቶች የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ግንባታውን ወጭ ይሸፍናሉ የተባሉት  ድርጅቶች ናቸው፡፡

የታንዛኒያ እና ኡጋንዳ አዲሱ የፍተሻ ጣቢያ በሁለቱም ሀገራት እንዲተዳደር ሲሆን ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ነው የተባለው፡፡

በመኪና የሚጓጓዙ ስደተኞች ፣የመንግስት ሰራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከባድ የጭነት መኪኖች  ከዚህ ቀደም የይለፍ ፈቃድ የሚያገኙት በሁለቱም ሀገራት ውስጥ ነበር ፡፡

በጋራ የሚያስተዳድሩት አዲሱ ፕሮጀክታቸው ግን  ይህ በሁለቱም ወገን ይሰጥ የነበረን አገልግሎት አንድ ማድረጉ ሲንዛዛ በነረው አገልግሎት ይጠፋ የነበረውን ግዜ በማስቀረት  የሸቀጥ ልውውጣቸውን ከፍ  ያደርጋል፡፡

በተጨማሪም ውጤታማ የድንበር ላይ ጥበቃ ዘዴን ለመዘርጋት የሚያስችል ሆኖ የትራንስፖርት ወጭንም ይቀንሳል፡፡ለፍተሻ ይወሰወድ የነበረውን ግዜ በሰላሳ  በመቶ እንደሚቀንስ በፕሮጀክት ጥናቱ ላይ ተገልጿል፡፡

ፕሮጀክቱ እውን በሚሆንበት አከባቢ ያሉ አብዛኛው የታንዛኒያ አከባቢዎች መብራት ተጠቃሚ አይደሉም፡፡  የፕሮጀክቱ መምጣት ለበርካታ የታንዛኒያ  ትንንሽ መንደሮች መብራት የማግኘት ተስፋን ይዞ መምጣቱ  ነው የተነገረው ፡፡

በቪክቶሪያ ሀይቅ አቅራቢያ ሙቱኩላ የተባለው ስፍራ የሚገነባው የጋራ ፍተሻ ጣቢያ ከታንዛኒያ መዲና ዳሬሰላም 1441 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ  ይገኛል ሲል የዘገበው ዘ ሞኒትር ነው፡፡