ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ መዘጋጀታቸውን አስታወቁ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ሁኔታዎች ከተመቻቹላቸው ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ መዘጋጀታቸው ተነግሯል፡፡

በተለያዩ ጊዚያት ከሙስና ቅሌቶች ጋር የሚያያዘው ፕሬዚደነት ዙማ በዚህ ሳምንት ሊያደርጉ የታቀደው ዓመታዊ ቁልፍ ንግግራቸው እንዲራዘም መደረጉ ከሥልጣን ለመልቀቅ ስለመዘጋጀታቸው አመላካች ነው በሚል ዘገባዎች እየቀረቡ ይገኛሉ ፡፡

የደቡብ አፍሪካ ገዥው ፓርቲ አፍሪካን ናሽናል ኮንግሬስ (ኤኤንሲ) ሊያደርግ የነበረው ዓመታዊ ጉባኤውን አራዝሟል፡፡ ፓርቲው ስብሰባውን ያራዘመበት ምክንያትም በፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የወደ ፊት እጣ ፈንታ ላይ ለመምከር መሆኑም እየተነገረ ነው፡፡

ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ሳምንት በዕለተ ሃሙስ ሊያደርጉ የነበረውን ዓመታዊ ንግግራቸውን አስቀድሞ ዛሬ ፓርቲያቸው ኤ ኤን ሲ በኬፕታውን ተገናኝቶ የ75 ዓመት አዛውንቱን የጃኮብ ዙማን ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳው እንደሚያደርግ ተዘግቧል፡፡

ዙማ ደቡብ አፍሪካን በሙስና ስለመዘበራቸው እና ሀገሪቱን እያጋጠማት ላለው የኢኮኖሚ መዳከም ሥልጣናቸውን ስጋት ላይ ከሚጥልባቸው ጉዳዮች አንዱ ነው ተብሏል፡፡

ሚስተር ዙማ ባሳለፍነው ወርሃ ታህሳስ የገዥው ኤኤን ሲ ፓርቲ የኃላፊነት ቦታቸውን በምክትላቸው ሲሪል ራማፎዛ ከተነጠቁ ወዲህ ተሰሚነታቸው በእጅጉ ተዳክሞ ታይቷል፡፡

የፕሬዝዳንት ዙማ የፕሬዝዳንትነት ሥልጣናቸው እ.ኤ.አ በ2019 አጋማሽ ላይ የሚጠናቀቅ ቢሆንም እየመጣባቸውን ያለውን ጫናዎች ግን እስከዛም በሥልጣናቸው ለመቆየታቸው ምንም ዋስትና እንደሌላቸው በመዘገብ ላይ ነው፡፡    

ፕሬዝዳንቱ እስከ 10 ቀናት ባሉ ጊዜያትም ብሔራዊ የበላይ ኮሚቴ በጉዳያቸው ከመከረ በኋላ ከሥልጣናቸው እንደሚያሰናብታቸው ተጠብቋል፡፡

የኤኤንሲ ፓርቲ ዋና ፀሃፊ አኬ ማጋሹሌ ለመገናኛ ብዙሃን እንደተናገሩ የዓመታዊ ስብሰባው የተራዘመበት ምክንያት በፕሬዝዳንት ዙማ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ መሃል ያለው የሥልጣን ሽግግር ሰላማዊ እንዲሆን የመነጋገር ጊዜን ለመግዛት መሆኑን አንስተዋል፡፡

የደቡብ አፍሪካ ዘታይምስ ይፋ ያልተደረገውን ምንጭ ጠቅሶ እንደዘገበው ሁሌቱ ሰዎች መሃል የቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ላይ ከስምምነቱ ከተደረሰ ዙማ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ተዘጋጅተዋል፡፡

የፕሬዝዳንት ዙማ እና ምክትላቸው ራማፎዛ ውይይትን የተከታተሉ ሚስቴር ማጋሹሌ ይህንኑን ከማረጋገጥ ቢቆጠቡም ሌሎች የኤኤንሲ መሪዎች እንደ የዚምባብዌው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሁሉ ፕሬዝዳንቱ ዙማም ክብራቸው ተጠብቆ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ እየተሠራ መሆኑን ይፋ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

ዙማ የነጮቹ የአፓርታይድ አገዛዝ በደቡብ አፍሪካ ካበቃበት እ.ኤ.አ ከ1994 በኋላ በከፍተኛ አወዛጋቢነት ሥልጣን ላይ የሰነበቱ መሪ ናቸው፡፡ ዙማ በርካታ የሙስና ቅሌቶች የሚነሱባቸው መሪ ሲሆኑ እሳቸው ግን ይህንንም ያስተባብላሉ፡፡                 

ለማንኛውም የኤኤንሲ የመጪው ዕረቡ ስብሰባ በልዩ ትኩረት የሚጠበቅ ነው፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ሚስቴር ዙማ ሥልጣናቸውን በድርድር የማይለቅ ከሆነ በዚሁ የካቲት ወር በሚሠጠው የመተማመኛ ድምጽ ዙማ ሥልጣናቸውን በግዴታ እንዲያስረክቡ የሚገደዱበት ሄኔታ ይፈጠራልና ነው፡፡

በደቡብ አፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪው የነልሰን ማንዴላ ፋውንዴሽን እና በሀገሪቱ ትልቅ ብሔር የዙሉ ንጉስ ጉድዊል ዝዌልቲኒ ዙማ ሥልጣናቸውን እንዲለቁ መክሯል፡፡( ምንጭ:ዘኢንዲፐንደንትና  አልጀዚራ)