ኬንያ ከ 32 ዓመታት በኋላ ስርዓተ ትምህርቷን ቀየረች

ኬንያ ከ 32 አመታት በኋላ የትምህርት ካሪኩለሟን/ስርዓተ ትምህርቷን  መቀየሯ ተገልጿል፡፡

አዲሱ የትምህርት ካሪኩለም  ተግባር ላይ፣ቴክኖሎጂ እና ተስጥዖን ማጎልበት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ መሆኑ ታውቋል፡፡

ኬንያ ለህጻናቷ ይበጃል አብዮትም ያመጣል ያለችውን አዲስ ስርዓተ ትምህርት  አስተዋውቃለች፡፡

የኬንያ መምህራንም ከ32 አመታት በኋላ አዲስ የትምህርት መስጫ ዘዴን እንዲተዋወቁ መንግስታቸው  አብቅቷቸዋል፡፡

ተግባር ላይ፣ቴክኖሎጂ እና ተስጥዖንበ ማጎልበት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸውን የትምህርት ካሪኩለም መምህራን እና ወላጆችም አበጀ ብለው መቀበላቸውን ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡

ከዋና ከተማዋ ናይሮቢ ወጣ ብሎ በሚገኝ አንድ የመንግስት ት/ቤት የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ እውን እየሆነ ነው፡፡

በቀጣይ አመትም  ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆን ልምድ እየተገኘበት እነደሆነም  ነው የተገለጸው፡፡

ከ 32 አመታት በኋላ በአዲስ መልክ ተግባር ላይ አትኩሮ የተቀረጸው ስርዓተ ትምህርት በሃገሪቱ የመማር ማስተማር ሂደት ውስጥይታዩ የነበሩትን ችግሮች ይቀርፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አልጀዚራ የዘገባው ምንጭ ነው፡፡