ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አል-በሽር የደቡብ ሱዳን ድንበር እንዲከፈት አዘዙ

የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አል-በሽር  የደቡብ ሱዳን ድንበር እንዲከፈት አዘዋል፡፡

ፕሬዚዳንት አል-በሽር ከደቡብ ሱዳን ጋር ያላቸውን ድንበር በአውሮፓዊያኑ 2011 ከተዘጋ በኋላ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ አሁን እንዲከፈት ያዘዙት፡፡

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም በደቡብ ሱዳን የተኩስ አቁም ቡድን ውስጥ የሚገኙትን ወታደሮች ከድንበር አቋርጠው እንዲወጡ መጠየቃቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው የድምበርና የነዳጅ ምርት የሚገኝበት ስፍራ የባለቤትነት ጥያቄ የሚነሳበት በመሆኑ በተፈጠረው አለመግባባት እ.አ.አ ከ2012 ጀምሮ በዳርቻው ላይ  ሁለቱ ሀገራት የነበራቸው ቁርሾ እልባት ሳያገኙ  አመታትን ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ደቡብ ሱዳን ለ22 ዓመታት ያህል ስትታመስ ከነበረችበት የእርስ በእርስ ጦርነት በ2005 በተደረገው ስምምነት አማካይነት ነፃ በመውጣት ከ2013 ወዲህ እራሷን ማሰተዳደር ችላለች፡፡ ይሁን እንጂ ሀገሪቱ በየግዜው በሚያጋጠሙአቸው የእርስ በርስ እና የሽብር ጥቃቶች መረጋጋት ርቆአቸው ቆይቷል፡፡

እንደ ሀገሪቱ የዜና ጣቢያ ሱና ዘገባ ፕሬዝዳንት አልበሽርና የሀገሪቱ ባለስልጣናት የሁለቱ ሀገራትን ድንበር ክፍት ለማድረግ ውሳኔን አስተላልፈዋል፡፡

ባሳለፈፍነው  ሳምንት ፕሬዝዳንት አልበሽር ድንበራቸውን ለደቡብ ሱዳን ክፍት በማድረግ  ሀገሪቱ  የነጋጅ ዘይት ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በሀገራቸው ያሉ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ለመገልገል የምትከፍለውን ክፍያም ዝቅ ሊያደርጉላት ተስማምተዋል፡፡

ከ2011 በፊት ደቡብ ሱዳን አብዛኛውን  የሱዳን የነዳጅ ዘይት ሀብት ያለበትን መሬት ትይዝ ነበር፡  ነገር ግን  በአውሮፓዊያኑ 2013 በአገሪቱ በተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት አማካይነት  ሀገራቱ ድንበር በሁለት ተከፍሏል፡፡  በዚህም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳናን እና  ሱዳን ዜጎች  ወደ ጎረቤት ሀገራት ተሰደዋል፡፡

ፕሬዚዳንት አልባሽር ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጋራ ድንበራቸውን  ክፍት ማድረጋቸው ሁለቱ ሀገራት የድንበር ንግድ ለመጀምር  እንደሚረዳቸውም ነው የገለጹት፡፡

ድንበሩን ክፍት ማድረግ የሁለቱ ሀገራት ዜጎች እንደፈለጉ በመንቀሳቀስና ንግዳቸውን ማከናወን እዲችሉ ለማስቻል ያለመ ነው ሲሉ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በካርቱም በተካሄደው የሰላም ስምምነት ወቅት ነው ፕሬዝዳንት  አልበሽር  የገለጹት፡፡

የደቡብ ሱዳናውያኑ መሪዎች ወደ ሀገራቸው  ገብተው  እንዲሰሩ  ፍቃደኛ መሆናቸው ሲገልጹ "እኛ  የሁለት ሀገራት ዜጎች ብንሆንም  ደቡብ ሱዳናውያን ወንድሞቻችን በመሆናቸው  ከእነሱ ጋር መቆም እና እነርሱን መርዳት ያስደስተናል ሲሉም ፕሬዝዳንት አልበሽር አክለዋል፡፡ (ሱና)