በአሜሪካና ሩሲያ ፕሬዝዳንቶች መካከል ሲራዘም የቆየው ስብሰባ ሊከናወን ነው

በአሜሪካና ሩሲያ ፕሬዝዳንቶች መካከል ለረጅም ጊዜ ሲራዘም የቆየው ስብሰባ እንዲከናወን  ሀገራቱ በመርህ ደረጃ እንደሚቀበሉት መሪዎቹ አስታውቋል፡፡

ሞስኮና ዋሺንግተን በፕሬዝዳንቶቻቸው መካከል ለማከናወን ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ስብሰባ መዘግየት እንዲያበቃ ሁለቱ ሀገራት በመርህ ደረጃ መሰማማታቸው ተገልጿል፡፡

ውሳኔው የተላለፈው የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንንት አማካሪ ጆን ቦልተን በሞስኮ ከፑቲን መገናኘታቸውን ተከትሎ መሆኑ ታውቋል፡፡

ትራምፕ በላኩት መልዕክት መሰረትም  በሚቀጥለው ወር በብራዝልስ ከሚደረገው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ስብሰባ ማግስት መሆኑን ቢቢሲ በዘገባው አስፍሯል፡፡

ምናልባትም ስብሰባው በደቡባዊ ፊንላንድ ዋና ከተማ ሄልሲንኪ ሊደረግ እንደሚችል ትራምፕ ፍንጭ ሰተዋል፡፡ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ መሰረትም በሶሪያ ስላለው ጦርነትና ከዩክሬን ጋር በተያያዘ ከፑቲን ጋር አንደሚነጋገሩም ገልፀዋል፡፤

ትራምፕና ፑቲን ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት በእስያ ፓሲፍክ ጉባኤ ወቅት መሆኑን ያስታወሰው ዘገባው በቀጣይ በመሪዎቹ መካከል የሚደረገውን ስብሰባ አስመልክቶ አስቀድሞ የተወሰነ መሆኑን ፍንጭ የሰጡት የክሬሚሊን ውጪ ጉዳይ አማካሪ የሆኑት ዩሪ አሽኮቭ ናቸው፡፡

ለሁለቱም መሪዎች ገለልተኛ የሆነችው ሀገር ፊንላንድ ለስብሰባው መመረጧን የተቀሱት አማካሪው የቦታና ሰዓት ጉዳይ በቀጣይ እንደሚገለጽ ተናግረዋል፡፡

ሆኖም በሩሲያ የተገኙት ቦልተን በሞስኮ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መሪዎቹ በመጪው ሳምንት እንደሚገናኙ ገልፀዋል፡፤

አክለውም ወደ ሞስኮ ከማቅናታቸው አስቀድሞ ፕሬዝዳንት ትራምፕ የሩሲያን ባለስልጣናት ስብሰባው በሚሳካበት ሁኔታ ላይ እንዲያወያዩ አንደላኳቸው ገልፀዋል፡፡

ፑቲንም ሆኑ ትራምፕ ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት መካከል መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ሊጠቀሙበት አንደሚችሉ ቦልተን ሀሳባቸውን አጋርተዋል፡፡

ችግሮቻቸውን ተቀራርቦ ከመነጋገር ባሻገርም በትብብር በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ይመክራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በሁለትዮሽ ግንኙነትም ሰፊ ምክክር ያደርጋሉ ብለዋል፡፡

በዚህም በመካከላቸው የሰፈነውን ውጥረት ያረግባሉ ብዬ አምናለው ሲሉ የዋሺንግተን ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጆን ቦልተን ተናግረዋል፡፤

በጉዳዩ ላይ ከቦልተን ጋር በተገናኙበት ወቅት አጭር ነገር ያሉት ፑቲን ከአሜሪካ ጋር ያላቸው ቁርሾ እንደሚፈታ ተስፋ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

በመካከላቸው ያለው ውጥረት ረገቦ ፈር አንደሚይዝም ያወሱት ፑቲን ሞስኮ ለጥረቱ መሳካት እንደምትተጋና ለተፈጠረው የላላ ግንኙነት መነስኤው ራሷ አሜሪካ በሌሎች ላይ የምታራምደው ያልተገባ የፖለቲካ ግፊት መሆኑን ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡