የአፍሪካ ክብር ጉባኤ ሁለት የአፍሪካ መሪዎችን ሸለመ

አዲስ አበባ ሐምሌ 23/2008(ዋኢማ)- የአፍሪካ ክብር ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝንና የሱዳኑን ፕሬዝዳንት ኡመር ሃሰን አልበሽርን ሸለመ።

የአፍሪካ ክብር ጉባኤ "ክብራችን በእጃችን" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 18 እስከ 22 ቀን 2008 . ሲካሄድ ቆይቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ለሽልማት የበቁት በአፍሪካ ለሚከሰቱ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ላበረከቱት አስተዋዕኦ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በጉባኤው መጠናቀቂያ ላይ ባለመገኘታቸው ሽልማቱን የፌዴራልና የአርብቶ አደር ጉዳዮች ልማት ሚኒስትሩ አቶ ካሳ ተክለብርሃን ተቀብለውላቸዋል።

የሱዳኑ ፕሬዘዳንት ኡመር ሀሰን አልበሽር ደግሞ የአፍሪካን ሉአላዊነት የሚገዳደሩ ተቋማት በአፍሪካዊያን ላይ የመወሰን ስልጣን እንዳይኖራቸው ባበረከቱት ሚና "የአፍሪካ ክብር ሻምፒዮን" በሚል ተሸልመዋል።

ፕሬዘዳንቱ በሽልማት ስነ ሥርአቱ ላይ ባደረጉት ንግግር "አፍሪካዊያን ለነጻነታችን ዋጋ እንደከፈልነው ሁሉ የተከበረችና የበለጸገች አፍሪካን ለመፍጠር በቅንጅት መስራት ይኖርብናል" ብለዋል።

የአገራት መሪዎች ህብረቱ የፈረማቸውና ያጸደቃቸው የሰብአዊ መብት ህጎችን በማጽደቅ፣ለአህጉርና ክፍለ አህጉር ድርጅቶች አቅም መጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።

የፌዴራልና የአርብቶ አደር ጉዳዮች ልማት ሚኒስትር አቶ ካሳ ተክለብርሃን በበኩላቸው "ለአፍሪካ ችግሮች ከአፍሪካዊያን ውጭ ቀዳሚ የመፍትሄ አካል ሊኖር አይችልምና በትብብር መስራት ይኖርብናል" ብለዋል።

የአፍሪካ ክብር ጉባኤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣በአፍሪካ የሰላምና ግጭት ጥናት ቅንጅት ኢንስቲትዩት፣በመንግስታቱ ድርጅት የሰላም ዩኒቨርሲቲና ሌሎች የአፍሪካ ተቋማት ጋር የሚዘጋጅ አህጉራዊ ጉባኤ ነው።(ኢዜአ)