የአየር ብክለት በአፍሪካ በየአመቱ ከ700 ሺህ በላይ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው

የአየር ብክለት በአፍሪካ አህጉር የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ነው ተባለ።

በአህጉሪቱ በአመት በአማካይ ከ700 ሺህ በላይ ዜጎች በአየር ብክለት የተነሳ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑም ተገልጿል።

ይህም በአህጉሪቱ ባልተመጣጠነ ምግብ እና በውሃ ብክለት ከሚሞቱ ዜጎች የበለጠ ሆኗል።

በአፍሪካ በውሃ ብክለት ብቻ በአመት 500 ሺህ ገደማ ዜጎች ይሞታሉ።

የአየር ብክለት አፍሪካን ዜጎቿን ብቻ ሳይሆን በአማካይ በአመት ከ230 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ገንዘብም ያሳጣታል።(ኤፍ.ቢ.ሲ)