ፖፕ ፍራንሲስ ለደቡብ ሱዳን ተጎጂዎች የዓለም ማህበረሰብ እጁን ሊዘረጋ እንደሚገባ ጥሪ አቀረቡ

የካቶሊኩ መሪ ፖፕ ፍራንሲስ የዓለም ማህበረሰብ ለደቡብ ሱዳን ተጎጂዎች የሚውል 500 ሚሊዮን  ዶላር ድጋፍ እንዲያደርግ ተማፅኖአቸውን አቅርበዋል፡፡

በፖፑ የሚመራ ኢንተግራል ሂይማን ዴቨሎፕመንት የተባለው ተቋም ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተገኙት ፖፕ ፍራንሲስ በደቡብ ሱዳን ትምህርት  ቤት የጤና ተቋማት እናመሰል ተቋማት መኖር ቢገባቸውም አሁን ባለው አለመረጋጋት ሊኖር አልቻለም  በዚህም ዜጎቹ ለአስከፊ አደጋ ተጋላጭ ሆነዋል ይላሉ፡፡

የዓለም ሀገራት ረጂ ድርጅቶች በደቡብ ሱዳን ያለውን የዜጎች እንግልት እና አስከፊ ርሀብ በመመልከት እጃቸውን ሊዘረጉ ይገባል ብለዋል ፖፑ፡፡  አሁን ላይ ደቡብ ሱዳንያውያን በእርስበርስ ግጭት እና ስላም ማጣት እጅጉን ተጎሳቁለዋል ብለዋል፡፡ 

ስደቱ እንዳለ ሆኖ ፋታ የማይሠጠው ርሃብ ግን የደቡብ ሱዳናውያን ትልቁ ስጋት ሆኗል፡፡ ፖፑ በዓለም ላለው አለመረጋጋት እና ሰላም ማጣት በዋናነት የራስ ስሜትን እና ጥቅም ማስጠበቅ ቅድሚያ በመሠጠቱ ስለሆነ መቻቻልን እና መስማማትን ማጎልበት አለብን ብለዋል፡፡

በደቡብ ሱዳን 2 ሚሊዮን ሰዎች በድርቅ እና አደገኛ ረሃብ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታም የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ በሀገሪቱ 6 ሚሊዮን ሰዎች በሳምንታት ልዩነት ለተመሳሳይ ችግር ታጋላጭ ይሆናል ተብሏል፡፡

አሁን ሊሰበሰብ ከታቀደው 500 ሚሊዮን  ዶላር በተጨማሪ ለትምህርት ለጤና እና ለግብርና የሚውል የገቢ ማሰባሰብያ እንደሚደረግም ታውቋል፡፡