በግሪኳ የኮስ ደሴት ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

በሬክተር እሰኬል ስድስት ነጥብ ሰባት የተለካ ርእደ መሬት በሜዲተራኒያንን ባህር ውስጥ የሚገኙ ሁለት የግሪክና የቱርክ ደሴቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተሰማ፡፡

በግሪኳ ኮስ እና በቱርኳ በድረም ተብለው በሚጠሩ ሁለት ደሴቶች ማህል የተከሰተው ርእደ መሬት በግሪኳ ኮስ ቤቶችን ያፈራረሰ ሲሆን በቱርኳ በድረም ደግሞ ደሴቲቷን በውሀ አጥለቅልቋል፡፡

የኮስ ከንቲባ ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ በርደ መሬቱ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ሁለቱ ደሴቶች በአውሮፓ ቱሪስቶች እንደሚዘወተሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአካባበው የሚገኙ ቱሪስቶች አካባቢውን ለቀው ለመውጣት በመጣደፍ ላይ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡