የኤርትራውያን ህፃናት ስደተኞች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ድርጅቱ አስታወቀ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያወጣው መረጃ በጣልያን የስደተኞች ጣቢያ ብቻ ወደ 25 ሺህ የሚጠጉቤ ተሰቦቻቸው በውል የማይታወቁ ህፃናት እንደሚገኙ አስታውቋል ፡፡

በርካቶች ከቤትንብረታቸው፣ ከዘመድወዳጆቻቸው፣ ከሚወዷት ሀገራቸው ተገፍተዋል፤ ተባረዋል፣ ታስረዋል፣  ተሰደዋል ብሏል ፡፡

እጅጉን የሚያሳዝነው ደግሞ ነብስ ያላወቁ ህፃናት ባህሩን፣ ዱሩን፣ ገደሉን አቋርጠውና ሞትን ታግለው ሊያሸንፉ ሲታትተሩ ማየት መሆኑን ነው የገለጸው ፡፡ 

ከላይ እንደማዓት የሚወረድ ብርቱ ፀሀይ ከታች እንደረመጥ የሚፋጅ ደረቅ መሬት ፤ፊትን ቆራርጦ የሚሄድ ወበቅ ያለው ደረቅ ንፋስ ብቻ በርካታ ፈተና ያለበት ስደት በኤርትራ ዜጎች ላይ እንደሚበረታ አመልክቷል ፡፡

ከሁሉም በላይ በህፃናትና በታዳጊዎች መሆኑ ታዲያ ያሳዝናል ነው ያለው ፡፡

የተባበሩት መንግስታ ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በጣልያን የስደተኞች ጣቢያ ወደ 25 ሺህ የሚጠጉ ቤተሰቦቻቸው በውል የማይታወቁ ህፃናትአሉ፡፡

በርካቶች እንደሚስማሙት የኤርትራውያን ስደት መንስኤ በሀገሪቱ ከሚስተዋለው ድህነት ባለፈ ፤ የፖለቲካ አለመረጋጋትና ጭቆና በዋናነት ጠቅሷል ፡፡

ሁሉም ህፃናትና ታዳጊዎች እንደሚናገሩት ከሆነ መማር ሲገባቸው በግዳጅ ወደ ውትድርና መግባታቸው ሲሆን፤ ካልገቡ ደግሞ በግዳጅ የተለያዩ የጉልበት ስራዎችን እንዲሰሩ መገደዳቸው እና ሌሎችም ምክንያቶች ለስደት በምክንያትነት ይገልጻሉ፡፡

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በየዓመቱ 400 ሺህ ወጣቶች እና ህፃናት ለውትድርና እና ለጉልበት ስራ ይታጫሉ ፡፡

ከጭቆናው ሽሽት ከጀመሩ ኤርትራውያን ባለፈው ዓመት ብቻ 10 ሺዎቹ ጥቃት ደርሶባቸው 2 ሺዎቹ ብቻ ሊቢያን መሻገራቸውን አስታውቋል ፡፡  

በተመሳሳይ በግብፅ በኩል ለመሻግር የሞከሩ 8 ሺህ ኤርትራውያን ለተለያየ ችግር መዳረጋቸውን ነው ያመለከተው ፡፡

ዜጎቹ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ ሀገራት እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት መጠለያዎች ቀሪ ጊዜያቸውን እየገፉ ሲገኙ ቀሪ ዜጎችም ባገኙት አጋጣሚ ከሀገር ለማምለጥ እና ከጭቆናው ገፈት ላለመቅመስ ወደ ውጭ ማማተራቸውን ቀጥለዋል ብሏል ፡፡