ጃፓን 3.7 ሚሊዮን የታሸገ የመጠጥ ውሃ ምርቶቿን ከገበያ ላይ ልትሰበስብ ነው

በፈረንሳውያን ባለቤቶች የሚመራው ቮልቪክ የምግብ አምራች ኩባንያ የሚያመርተው ቮልቪክ የመጠጥ ውሃ፤ ከጃፓን  ገበያ እንዲሰበሰብ ነው ትዕዛዝ ተላለፈ ፡፡

የመጠጥ ውሃ አምራቹ ከፈረንሳይ የሚያስመጣቸው የማሸጊያ ፕላስቲኮቹ ጥራት ጉድለት እና የተመረተው ውሃ የተመጣጠነ የንጥረ ነገር ውህደት የለውም በሚል የጃፓን ምግብ እና ምግብ ነክ ጉዳዮች ጤና ተቆጣጣሪ ተቋም የሽያጭ እገዳውን አስተላፏል፡፡

የፕላስቲኮቹ  የአገልግሎት ዘመን ማብቂያ እኤአ በ2019 ቢሆንም ቅዝቃዜና ሙቀትን ለመቋቋም በሚያስችል መልኩ አልተመረቱም ተብሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የፕላስቲክ ጠርሙሶቹ ጫፍ ጉዳት እንደሚያስከትሉም ነው ተቋሙ ገልጿል፡፡

ቮልቪክ የማዕድን ውሃ አምራች በመሆኑ በምርቶቹ ውስጥ የተመጣጠነ የንጥረ ነገር ውህድ  አላገኘሁም ብሏል ተቋሙ፡፡

ይህም ለሰዎች ጤና ጠንቅ በሆነ መንገድ ተመርቶ ለገበያ በቅቷል ነው ተመልክቷል ፡፡

በዘንድሮው ዓመት በፋብሪካው ከተመረተው ውስጥ 3.7 ሚሊዮን የሚሆነው የታሸገ የመጠጥ ውሃ ከጃፓን  ገበያ ላይ እንዲሰበሰብ ነው የተባለው፡፡

ይህም በጃፓን የውሃ  ገበያ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዝ ተነግሯል፡፡

ቮልቪክ እንዲህ አይነቱ ክስተት ሲፈጠርበት የመጀመሪያው እንዳልሆነ ሲነገር ከዚህ በኋላ ለሚፈጠረው ማንኛውም አይነት መሰል ጥፋት ምርቱን እስከማቋረጥ እርምጃ እንደሚወሰድበትም ተነግሯል፡፡

ድርጅቱ በጃፓን የምርት ሽያጩን ማቅረብ የጀመረው እኤአ በ2002 ነው፡፡

የአሁኑ ውሳኔም ተቋሙን ለከፍተኛ ኪሳራ እንደሚዳርገው ጠቅሶ የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡ (ምንጭ:  ቢቢሲ)