ቻይና በአገር ውስጥ የገጣጠመችው የመንገደኞች አውሮፕላን በተካካ ሁኔታ በረራውን አካሄደ

ቻይና ሙሉ ለሙሉ  በአገር ውስጥ ግብዓቶች  የገጣጠመችው የመንገደኞች አውሮፕላን የመጀመሪያ  በረራውን በተሳካ ሁኔታ  ማከናወኑን  አስታወቀ ።   

ቻይና ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ የገጣጠመችው የመንገደኞች አውሮፕላን ሲ 919  የተባለ   የመንገደኞች አውሮፕላን  ሲሆን  በቻይና ከዚህ  ቀደም  ከተገጣጠሙት አውሮፕላኖች  በትልቅነቱ ቀዳሚውን ሥፍራ ይይዛል ።

አውሮፕላኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ያከናወነውን በረራ በድል ማጠናቀቁን ያስታወቀው ኮማክ የተባለው የአውሮፕላን አምራች ተቋም ቻይና በአቬሽን ኢንዱስትሪው  ከቀዳሚዎቹ ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ የሚያስችላትን እርምጃ ጀምራለች ብሏል፡፡ 

ሲ919 አውሮፕላን ታዋቂዎቹ ኤር ባስ እና ቦይንግ ሳይፀነሱ በእቅድ ተይዞ የቆየና በቀላሉ ሊጠገን በሚችል መልኩ ዲዛይን የተደረገ እንዲሁም በመጠነኛ ወጪ ወደ ተግባር የተሸጋገረ መሆኑንም ነው ተቋሙ ያስታወቀው፡፡

በአውሮፓና አሜሪካ ተግባራዊ የተደረጉ የደህንነት መመሪያዎችን በሚገባ አሟልቶ ወደ አቬየሽኑ ገበያ ብቅ እንዳለ የተነገረው አውሮፕላኑ፤ከቻይና ውጪ ባሉ ሀገራት ለመሸጥ የሚያስችለውን ፈቃድ ግን መጠባበቅ ግድ ይለዋል ነው የተባለው፡፡

ይህ ጉዳይ ግን ከ40 ዓመታት በፊት በድህነት ስትማቅቅ ለነበረችው አሁን ላይ በምጣኔ ሃብት እድገቷ በዓለም ሁለተኛ ደረጃን ተቆናጣ ለምትገኘው ቻይና ምንም አይነት  ምን ያህል  ከባድ እንደነበረ ማስተዋል አይከብድም ፡፡

አሁን ግን  ሲ919 አውሮፕላን  መሠራት ከዓመት ወደ ዓመት እየተመነደገ ለሚገኘው የቻይና አቪዬሽን ኢንዱስትሪ ትልቅ የምስራች ተብሎ ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡

ይህ የቻይና አውሮፕላን የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ ምርት አይደለም፡፡በመሆኑም ነዳጅ ቆጣቢ ፣ ፈጣንና የደንበኞችን ምቾት ያስቀደመ መሆን ከቻለም የአሜሪካውን ቦይንግ ጨምሮ አንጋፋና አትራፊ የሆኑትን የአውሮፓ አውሮፕላን አምራቾችን በጥቂት ዓመታት ውስጥ ሊወዳደር እንደሚችልም ተገምቷል፡፡ ( ምንጭ : የኒወርክ ታይምስ)