ቻይና የወጪና ገቢ ንግድ እንቅስቃሴዋን በከፍተኛ ፍጥነት ማደጉ ተገለጸ

ከቅርብ አመታት ወዲህ ቻይና ከተለያዩ የአለም  ሀገራት ጋር የምታደርገው የንግድ እንቅሰቃሴ ከፍተኛ  ነው፡፡ለዚህም ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላት የንግድ ግንኙነት  ተጠቃሽ ነው፡፡

ታዲያ ሀገሪቷ እኤአ በ2017 ካስመዘገበችው የወጭ እና ገቢ ንግድ እንቅሰቃሴዋ በሰኔ ወር ያሰመዘገበችው ከፍተኛ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡

መረጃው እንደሚያትተው በግንቦት ወር ከተመዘገበው ወደ ውጭ የተደረገው የንግድ እንቅሰቃሴ 8ነጥብ 7 በመቶ የነበረ ሲሆን በሰኔ ወር ወደ 11ነጥብ 3 በመቶ ከፍ ብሏል ይህ ማለት 196ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በወሩ  ሀገሪቱ ማግኝት  ችላለች፡፡

በተመሳሳይ ወደ ሀገር ውስጥ የተደረገው የንግድ እንቅሰቃሴ በግንቦት ከነበረው 14ነጥብ 8 በመቶ ጋር ሲነፃፀር በ17 ነጥብ 8 በመቶ አድጓል በወሩ የ153ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር ተመዝግቧል ነው የተባለው፡፡   

ቻይና ባለፉት አሥርት አመታት በውጭ እና  ገቢ ንግድ ላይ ያደረገችው ጠንካራ የንግድ እንቅሰቃሴ አሁን ላይ የምጣኔ ሃብቷን ለመደገፍ እንዳገዛት ይነገራል፡፡

በተለይ ወደ ተለያዩ የአለም ሀገራ የሚደረጉ የንግድ እንቅሰቃሴዎች የሀገሪቷን የውጭ ምንዛሪ ገቢ ከፍ ሰላደረገው ለምጣኔ ሃብቱ የጀርባ አጥንት ሆኖ ቆይቷል ነው የተባለው፡፡

በተለይ ሀገሪቷ ሸቀጦችን እና ለእለት ተዕለት ፍጆታ የሚውሉ ነገሮችን በብዛት ወደተለያዩ ሀገሮች ሰለምትልክ  በአለም አቀፍ ደረጃ  ተፈላጊ ከሆኑ ሀገሮች ውሰጥ ቀዳሚ መሆኗ ይነገራል፡፡

ይህ ደግም የንግድ እና የኢንቨስትመንት እንቅሰቃሴዋ ላይ ተመራጭ እና ተፈላጊ ሀገር እንድትሆን ከማድረግ ባሻገር ሀገሪቷ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነትም መልካም እንደሚያደርገው ይታመናል ነው የተባለው፡፡

አለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላተው ምጣኔ ሃብታቸው በፍጥነት እያደጉ ካሉ ሀገራ መካከል ቻይና ቀዳሚውን እንደምትይዝ እና ከንግድ አጋሮቿ ጋር ያላትን ግንኝነት ይበልጥ ካጠናከረች ደግሞ የምጣኔ ሀብቷ በእጥፍ እንደሚያድግ ተገልጿል፡፡